ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ የአዲስ ማሽንና መለዋወጫ ማምረቻ ኢንዱስትሪ
በኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ የአዲስ ማሽንና መለዋወጫ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ከድርጅቱ
የሚወገዱ የተለያዩ የብረት ፍቅፋቂ (ችብስ) ፣ የኮፒውተር ካርትሪጅ፣ አሮጌ ጎማ እና የተቃጠለ ዘይት ከነበርሜሉበጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ተጫራቾች -
1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው
2. የግብር ከፋይነት የተመዘገቡና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN NO) ያላቸው
3. ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብየሚችሉ
4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ _ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውንማስረጃዎች ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋው 2% ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
6. ተጫራቾች የማይመለስ 300 (ሶስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታው ሙሉ ሰነድ በኢንዱስትሪው ንብረትአስተዳደር ቢሮ ዘወትር በስራ ሰዓት መውሰድ ይችላሉ፡፡
7. መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳችሁን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማሸግ በተዘጋጀውየጨረታ ሰነድ ጨረታው ከወጣበት እስከ አስራ ስድስተኛው ቀን አራት ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ትችላላችሁ፡፡
8. ጨረታው ለተከታታይ አስራ አምስት ቀን አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በአስራ ስድስተኛው ቀን የጨረታ ሳጥኑ 4፡30 ተዘግቶ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡45 ይከፈታል፡፡ መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡ ሜክሲኮ አደባባይ ወደ ሣር ቤት በሚወስደው መንገድ ከኦላ ኢንጅነሪንግ ወደ ውስጥ 100 ሜትር ገባብሎ ያለው ግቢ
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 25111508685/251115520565 ደውለው ቢጠይቁን መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
በኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ የአዲስ ማሽንና መስዋወጫ ማምረቻ ኢንዱስትሪ
