ለመኪና ኪራይ የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ሆማተ 2929/2016
በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የሆሣዕና ማረሚያ ተkም
የሆሣዕና ማረሚያ ተቋም የህግ ታራሚዎችን እና የፖሊስ ሰራዊቱን ተቋሙ ባዘጋጀው የድርጊት መርሃ ግብር መሠረት በየቀኑ ከጠዋቱ 12፡30-11.30 ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ ድረስ ቅዳሜና ዕሁድ ሳይካተት በሥራ ቀናት ከተማው ከ07 ኪ/ር ደርሶ መልስ ሰርቪስ አገልግሎት ሊሰጥ የሚችል እንዲሁም በሀገሪቱ ካላንደር መሠረት የሥራ ቀናት ዝግ በሚሆንበት በህዝባዊ በዓላት ቀናት ለምግብ ቤት ሠራተኞችና ለፖሊስ ሠራዊቱ መደበኛ ሰርቪስ አገልግሎት የሚሰጡ እና ከዚህ በታች በሠንጠረዡ ውስጥ የተመለከተውን መካከለኛ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ መስፈርቱን ከሚያሟሉ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን ግለሰቦችን/ ከሀምሌ 1/2016 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 30/2017 ዓ/ም ድረስ ለስድስት ወራት በሚቆይ የማዕቀፍ ሥምምነት በውል ሰጪና በውል ተቀባይ መካከል በሚደረገው የውል ሥምምነት መሠረት የሰርቪስ የአገልግሎት ጊዜውን
እንደአስፈላጊነቱ ከ10 ወር እስከ 06 ወራት ተጨማሪ ጊዜ ለማራዘም እንደሚቻል ታሳቢ ባደረገ መልኩ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የአገልግሎት ግዥ (የመኪና ኪራይ) ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የዕቃው/የአገለገሎቱ አይነት |
መለኪያ |
ብዛት |
|
01 |
44 እና ከዚያ በላይ ተሳፋሪዎችን የመጫን አቅም ያለው መካከለኛ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ |
በቁጥር |
01 |
መመዘኛዎች፣
1. በመስኩ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው/ላት፤ የዘመኑን ግብር የከፈለች፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው/ያላት እንዲሁም የ VAT 15% ተመዝጋቢ የሆነች፤ የመኪና ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ያለው/ያላት የባለቤትነት መታወቂያ (ሊብሬ/ ያለው ያላት፡፡
2. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ሆሣዕና ማረሚያ ተቋም ግዥና ፋይናንስ ንብ/አስ/የሥራ ሂደት ቢሮ በመቅረብ ለዚሁ ግዥ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በነፃ መውሰድ የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፤ የጨረታ ማስከበሪያን በሚመለከት የብር 5.000/አምስት ሺህ /ብቻ CPO ወይም ተመሳሳይ ዋስትና ሰነድ በማሰራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
3. ተጫራቾች:- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15/አሥራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ተሞልቶ ከሙሉ ሰነዶች ጋር እንዲሁም ከላይ በተራ ቁጥር oi የተዘረዘሩትን ማስረጃ ኮፒዎች ጋር በታሸገ ኤንቬሎፕ አዘጋጅተው ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የንግድና ሌሎች ኮፒ ማስረጃዎች ላይ አጠራጣሪ ነገሮች ከታየ ኦርጅናል ማስረጃዎችን አስቀርቦ የማጣራት እና የማረጋገጥ እንዲሁም ተጫራቾቹም ኦርጅናል ማስረጃዎችን የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
5 ጨረታው በ15ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት በማረሚያ ተቋሙ ግዥ ፋይ⁄ ንብረት አስተዳደር ቢሮ ወይም ተመሳሳይ አዳራሽ የሚከፈት መሆኑን ስንገልጽ፤ ዕለቱ የበዓላት /የዕረፍት/ ቀን ከሆነ በማግስቱ በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
6. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይንም በክፊል የመሰረዝ መቡቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0926517224 0912052832 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0926517224 0912052832 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ማረሚያ ቤቶች
አስተዳደር የሆሣዕና ማረሚያ ተkም
