Tender Detail

Tender Details

  • Deadline05 Jun 2024, 2:22 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Organizational

ለመጀመሪያ እና ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ


ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተገለጹትን እቃ አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚህ መሰረት-

ለመጀመሪያ ጊዜ ጨረታ የወጣ የአቃ/የአገልገሎት ገዥ

ሎት 1. የተባይ፣ የአይጥ መከላከያና ማጥፈያ መድሀኒት ርጭት አቅርቦት ግዥ፣

ሎት 2. የወተት አቅርቦት ግዥ፣

ሎት 3. የሻወር ጌት ቫልብ ግዥ፣

ሎት 4. የሮቤኔቶ /Robnato/ ግዥ:

ለሁለተኛ ጊዜ ጨረታ የወጣ የአቃ/የአገልግሱት ግዥ

ሎት 1. የአይብ አቅርቦት ግዥ

ተጫራቾች የሚከተሉትን መመሪያዎች ማሟላት ተገባራዊ ማድረግ አለባቸው፡፡

1. ተጫራቾች በዘርፋ የተሰማሩበት ሕጋዊና የታደሰ የ2016 ዓ.ም ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ TIN እና VAT ሰርተፍኬት ያላቸው፤ የገቢዎች ከሊራንስና ጨረታ ለመሳተፍ ከሀገር ውስጥ ገቢ የተሰጣቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢዎች ዝርዝር

የምዝገባ ፈቃድ የተመዘገቡና የቅርብ ጊዜ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

3. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ / CPO/ ከቴክኒካል ኦርጅናል ሰነድ ጋር አያይዘው መገኘት አለባቸው::

4. ለእያንዳንዱ ጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በድርጅታችን አዲሱ ፍልውሃ ሆቴል እንግዳ መቀበያ በመክፈል ከድርጅቱ ግዥ አቅርቦት ቡድን መሪ ቢሮ ቀርበው የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

5. ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊትና ከነቫቱ ተብሎ በኢትዮጵያ ብር የተገለጸ መሆን አለበት፡፡ ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውን፣ ፊርማቸውንና ማህተም

አሟልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡

6. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሠነድ ላይ የተሰጠ ዋጋን መለወጥ አይቻልም፡፡ ዕቃው የሚቀርብበት

ጊዜ፣ ቦታና ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ መገለጽ አለበት፡፡ ሰለ ዕቃው ዋስትናና የዋስትና ጊዜ በግልጽ

መገለጽ አለበት፡፡

7. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ለማሸነፍ እንዲረዳዎት ለማንኛውም ኃላፊና ሠራተኛ መደለያ የሰጠ ተጫራች ከጨረታ የሚሰረዝ ሲሆን አሸንፎም ውል ቢዋዋል ውሉ ይሰረዛል፡፡

8. ድርጅታችን የዋጋ ለውጥ ሳይኖር በመጠን ወይም በዋጋ እስከ 25% በመጨመር ወይም 20% በመቀነስ መግዛት እንደሚችል በቅድሚያ መታወቅ ይኖርበታል፡፡

9. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ከቫት በፊት ወይም ከቫት ጋር በግልጽ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 5 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው ጠዋት በዕለቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡

10. ተጫራቾች በሚጫረቱበትን የግዥ አይነት መሠረት የተሟላ የቴክኒካል ሰነድ እና ፋይናሽያል በተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ /Bid document/ መሰረት ጨረታ ሰነዳችሁን ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ የጨረታው ቴክኒካል ፕሮፖዛል ሰነድ ለብቻው የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ ለብቻው እና ፋይናሽያል ሰነድ ለየብቻው በጨረታ ሣጥኑ ማስገባ አለባቸው፡፡

11. የጨረታ ሂደቱ የቴከኒካል ግምገማ ድርጅቱ በሚያወጣው መስፈርት መሠረት ቴክኒካል ሠነድ ግምገማና እስፔስፊኬሽን (Specification) ግምገማ ውጤት (40%) እና የፋይናንሽያል (ዋጋ) ግምገማ ውጤት (60%) ሲሆን ድምር ውጤት ከ100% አሸናፊ የሚለይ መሆኑን ማወቅ አለባችሁ፡፡ ነገር ግን ቴከኒካል ግምገማ ሰነድ ወይም እስፔስፊኬሽን (Specification) ግምገማ ያላለፈ ተጫራች ድርጅት ፋይናንሽያል ሠነድ እንደማይከፈት እንዲታወቅ፡፡ የመገምገሚያ መስፈርቶቹ በሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ማየት ይቻላል፡፡

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 011-5-53-07-67/ 011-5-15-73-37

ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት

Save Tender