Tender Detail

Tender Details

  • Company እስኩል ኦፍ ቱሞሮ
  • Address , Phone: 0116 62-66-95
  • Website
  • Deadline23 May 2024, 6:01 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Organizational

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

እስኩል ኦፍ ቱሞሮ


ድርጅታችን ግንባታው የተጠናቀቀ የአንድ ህንፃ ዋጋ ትመና “Valuation” ለማሰራት የሚፈልግ በመሆኑ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማስራት ይፈልጋል::

ስለሆነም ከታች የተቀመጡትን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 23 ቀን 2016 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ 8፡00 ሰዓት ድረስ ባሉት የሥራ ቀናት ውስጥ የመጫረቻ ሰነዳችሁን እስኩል ኦፍ ቱሞሮ ኃላ.የተ. የግ.ማ. ቦሌ ቅርንጫፍ ቢሮ ቁጥር 106 ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን::

ጨረታው ተጫራቾች በተገኙበት በግንቦት 23 ቀን 2016 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ በ8፡30 ሰዓት በዚሁ በድርጅቱ ቢሮ የሚከፈትና አሸናፊውም የሚወሰን ይሆናል::

ተጫራቾች ለሥራው ክንውን ሂደት እንዲሁም ለምታቀርቡት ዋጋ እንዲያመቻችሁ ድርጅቱ ያዘጋጀውን “TOR” በስራ ሰዓት ከላይ በተጠቀሰው ቅርንጫፍ ቢሮ በመምጣት መውሰድ ትችላላችሁ::

➢ የሚያስገቡት የጨረታ ሰነድ በ2 ፖስታ የታሸገ ሲሆን አንዱ ቴክሊካል ፕሮፖዛል (አሰራሩን የሚገልፅ) ሁለተኛው ደግሞ ፋይናንሻል ፕሮፖዛል (ክፍያን በተመለከተ) መሆን አለበት::

➢ የሚያስገቡት ሰነድ በተሰጠው “TOR” ዝርዝር መሠረት ዋጋው መቀመጥ አለበት::

➢ በህንፃው ዋጋ ትመና ላይ የሚሳተፉትን ባለሙያዎች ፕሮፋይል አያይዞ ማቅረብ አለባቸው::

➢ የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን ወይም ከቫት በፊት ስለመሆኑ በግልፅ መግለፅ ይኖርበታል:: ነገር ግን ይህ ሳይሆን ሲቀር የሚቀርበው ዋጋ ቫትን ያካተተ እንደሆነ ተደርጎ ይወሰዳል::

➢ የታደሰ የሥራ ፈቃድና ከዚህ በፊት የዋጋ ትመና የሰሩበት ድርጅት የምስክር

ወረቀት ማያያዝ ይኖርባቸዋል::

➢ ድርጅቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

አድራሻ

እስኩል ኦፍ ቱሞሮ ቦሌ ቅርንጫፍ

ከቦሌ ድልድይ ወደ ቦሌ ሚካኤል በሚወስደው ቀለበት መንገድ ላይ ከአዲስ የልብ ህክምና ሆስፒታልን አለፍ ብሎ ወደ ቀኝ በሚያስገባው መንገድ 70 ሜ ገባ ብሎ

ለማንኛውም ጥያቄ በ0116 62-66-95 ይደውሉ

Save Tender