የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር ኢአጽ/ ግንአዳ/014/2016
Ethiopian Insurance Corporation (የኢትዮጵያ መድን ድርጅት)
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት አዲስ አበባ እና ከአዲስ አበባ ውጪ ለሚገኙ ቅርንጫፎች እና ዲስትሪክቶች ኤል.አዲ ቦክስ ላይት (LED Box light) ግዥ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል፡፡
1. በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸውና በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው ከድረ-ገፁ (Website) ዓትመው ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
2. ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡና የግብር መለያ ሰርተፍኬት ያላቸው መሆኑን የሚያጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
3. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለገሀር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም ለዘጠና ቀናት የሚቆይ ቅድመ ሁኔታ ያላስቀመጠ የባንክ ዋሰትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. ተጫራቾቾ መወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለገሀር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ግንቦት 23 ቀን 2016 ዓ.ም. እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በእለቱ ማለትም ግንቦት 23 ቀን 2016 ዓ.ም. በግዥና ንብረት አስተዳደር ማኔጅመንት የስብሰባ አዳራሽ ከቀኑ 8፡30 ይከፈታል፡፡
6. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
7. ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር፡-011-551 24 00 የውስጥ መስመር 237/262 ወይም በቀጥታ ስልክ 011- 550 49 31/011-551 70 77 መጠየቅ ይቻላል፡፡
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት
