የጨረታ ማስታወቂያ የግዥ መለያ ቁጥር፡ HU/CSH/NCB/Medical
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻሳይዝድ ሆስፒታል
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተለያዩ የፊዝዮቴራፒ እና የጥርስ ህክምና ዕቃዎችን የሚያቀርቡ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ ጋብዞ በማወዳደር ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡
1 ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ ከፌደራል ሀገር ውስጥ ገቢ ወይንም ከሌሎች ግብር ሰብሳቢ የመንግስት መ/ቤቶች ወቅታዊ የግብር ግዴታቸውን የተወጡና በመንግስት ጨረታዎች መካፈል የሚችሉ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ፤ በፌደራል ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የመረጃ መረብ ድረ-ገጽ /web site/ ላይ የተመዘገቡ እና የሚጫረቱበት ዋጋ ከብር 200.000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ የሚበልጥ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
2. ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ብር 40,000.00 (አርባ ሺህ) በተረጋገጠ ቼክ ወይም (CPO) የጨረታው ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
3, በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የተዘጋጀውን ሠነድ ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን መግዛት ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ ብቻ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ በሆስፒታሉ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
5, ጨረታው ግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ. ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ 8፡40 በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በሚገኘው መሰብሰብያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
6. ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር 251-462-12-13 79
ፋክስ 251-462-20-87-55
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ
ስፔሻሳይዝድ ሆስፒታል
