የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 028/2016
ኮምቦልቻ
የኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን ማህበር ዝርዝራቸው ከዚህ በታች የተገለጹትን የተለያዩ ዕቃዎች በዝግ ጨረታ መሰረት አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
1. የተለያየ መጠን ያላቸው የተጠናቀቁ የጨርቅ ተረፈ ምርቶች፤
2. የተለያየ አይነት የጥጥ ቅሪቶችና ተረፈ ምርቶች፤
3. የተለያየ አይነት ብረታ ብረት እና መለዋወጫ ዕቃዎች፤
4. የተለያየ መጠን ያላቸው የተጋቡ የፕላስቲክ ጀሪካኖችና የብረት በርሜሎች እንዲሁም ሌሎች ልዩ ልዩ ዕቃዎች
በጨረታው ማንኛውም በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለው ግለሰብ ወይም ድርጅት መሳተፍ የሚችል ሲሆን ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከአክሲዮን ማህበሩ ቅ/ጽ/ቤት አዲስ አበባ ወይም ከዋናው መ/ቤት /ኮምቦልቻ መግዛት ይችላሉ፡፡
ዕቃዎቹን ዘወትር በስራ ሰዓት ( ከሰኞ-ዓርብ ከ 2፡00 – 10፡00 እና ቅዳሜ ከ2፡00 -6፡ oo ሰዓት) ዋናው መ/ቤት ኮምቦልቻ እንዲሁም የተወሰኑትን ዕቃዎች ደግሞ በአዲስ አበባ የድርጅቱ መጋዘን ላይ በመመልከት የሚገዙበትን ነጠላ ዋጋ አ/ማህበሩ ባዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ በትክክል በመሙላት በሰም በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ
በጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በጨረታ መመሪያው ላይ የተገለጸውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ወይም በ (CPO) በማስያዝ ከላይ በተገለጹት ቦታዎች ላይ በመገኘት ዋጋ ማቅረብ
የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ የጨረታ ማስታወቂያው በተዘጋ በ 3ኛው ቀን ኮምቦልቻ/ወሎ/ በሚገኘው በዋናው መ/ቤት ከጠዋቱ በ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት
ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የህዝብ በአል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል፡፡
አ/ማህበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ-
(ኮምቦልቻ) ስልክ ቁጥር 033-5510627 / 5510211
(አዲስ አበባ) ስልክ ቁጥር 011-5530124 / 5511805
ራስ ደስታ ዳምጠው ጎዳና ፓፓሲኖስ ህንጻ 1ኛ ፎቅ
ኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን ማህበር
