የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር ብ/ግ/ጨ/10/2016
Debre Markos University (ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ)
የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በ2016 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተገለፁትን ማለትም፡-
ሎት1 - Different Toners
ሎት2 - Small and Medium Machines Spare Parts
ሎት3 - Heavy Duty Machines - Spare Parts
ሎት4 - ID card Printer with Lamination Module
Debre Markos University
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ዕቃውን ለማቅረብ የሚፈልጉ ተጫራቾች
1. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የቲን ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የታክስ ክሊራንስ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ማቅረብ የሚችሉ፣
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ዋጋ ሞልተው ሲመልሱ የጨረታ ማስከበሪያ ብር፦
- ለሎት 1 ብር 100,000.00/አንድ መቶ ሺህ/
- ለሎት 2 ብር 100,000.00/አንድ መቶ ሺህ/
ለሎት 3 ብር 100,000.00/አንድ መቶ ሺህ/
ለሎት 4 ብር 50,000.00/ሃምሣ ሺህ/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ
ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ስም አሠርተው ማቅረብ አለባቸው፤
3. አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ በተገለፀለት ከ7/ሰባት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በግንባር ቀርቦ አሸናፊ የሆነበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ በ8 ቀናት ውስጥ ውል መያዝ የሚችል መሆን አለበት፣
4. ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ሥራ ተቋራጮች ሁሉ የጨረታ ዶክመንቱን ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ህንፃ ቁጥር 27 ቢሮ ቁጥር 10 እና አዲስ አበባ አራት ኪሎ ከቅድስት ማርያም ቤተ-ክርስቲያን ወረድ ብሎ ሮሚና ካፌ _
ህንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 07 ድረስ በመቅረብ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት የማይመለስ ብር 300.00/ሦስት መቶ/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዩኒቨርሲቲው ስም በተከፈተው የሂሣብ ቁጥር 1000017980517 ከፍለው ደረሰኝ በማቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፤
5. ተወዳዳሪ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአግባቡ በመሙላትና በማሸግ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡59 ድረስ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ህንፃ ቁጥር 27 ቢሮ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀውቁጥር 10 ድረስ በመቅረብ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፤
6.ጨረታው በ22ኛውቀን ከጠዋቱ 4፡ዐዐ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ህንፃ ቁጥር 27 በግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች በጨረታው ላይ መገኘት ካልቻሉ መስፈርቱን እስካሟሉ ድረስ በጨረታው ላይ ያልተገኙ ተጫራቾች ፖስታን ጨምሮ ጨረታው በእለቱ ይከፈታል፡፡
7. የጨረታውን ፋይናንሽያል እና ቴክኒካል ኦርጅናል ዶክመንቶች እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያውን ለየብቻ አስተማማኝ በሆነ ማጣበቂያ በታሸገ ፖስታ በማድረግና በእያንዳንዱ ፖስታ ላይ የመ/ቤቱን ሙሉ ስምና አድራሻ በመፃፍ ማህተም በማድረግ በተጠቃለለ አንድ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ሲኖርባቸው ፋይናንሽያል እና ቴክኒካል ዶክመንቶች ከኦርጅናሉ በተጨማሪ አንድ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡፡
8. ዩኒቨርሲቲው ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡- የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀናት ከሆነ ጨረታው በቀጣዩ የሥራ ቀን ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል፡፡
በተለያዩ ሎቶች ላይ ተመሣሣይ ዕቃ ካለ ተጫራቾች ተመሣሣይ ዋጋ መሙላት አለባቸው
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 058-771-66-91 ደብረ ማርቆስ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ
