ሁለተኛ ዙር የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
Jinka Polytechnic College (የጂንካ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ)
የጂ/ፖ/ቴ/ኮሌጅ በ2016 ዓ.ም 2ኛ ዙር ለስልጠና አገልግሎት የሚውሉ የአውቶሞቲቭ፣ የኤሌትሪክ፤ የጋርመንት የስልጠና መሳሪያዎችና ባጃጅ በሃገር አቀፍ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ላይ ለመወዳደር/ለመሳተፍ የምትፈልጉ አቅራቢዎች፡-
1. አግባብነት ያለው የዘመኑ ንግድ ፈቃድ ያለው፦
2. የግብር ከፋይ የተመዘገበበት ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ከሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4. የዘመኑን የታደሰ የንግድ ሰርተፊኬት ማስረጃ እና በፋ/ኢ/ል/ቢሮ በአቅራቢነት የተመዘገቡበት ደብዳቤ ፎቶ ኮፒ በመያዝና የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመከፈል የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት የጂንካ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 203 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
5. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ጋር የጨረታ ማስከበሪያ በእያንዳንዱ ዘርፍ የ5000.0 ብር አምስት ሺህ ብር ብቻ) በህጋዊ ባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በማዘጋጀት የጨረታ ሰነድ አንድ ኦሪጅናልና ሁለት ኮፒ ፖስታዎችን ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፐ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
6. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ በተገለፁት የሎት ዓይነቶች በአንዱ ወይም በሁሉም መወዳደር ይችላሉ።
7. የመጓጓዣ ወጪ በተጫራቾች የሚሸፈን ይሆናል፡፡
8. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ በ10 (በአስር) ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) የውል ማስከበሪያ ሲፒኦ በማስያዝ ከመ/ቤቱ ጋር ውል በመፈፀም አሸናፊ የሆነባቸውን ዕቃዎች በሙሉ በ15 ቀናት ውስጥ በመ/ቤቱ ቅጥር ግቢ ንብረት ክፍል ድረስ በመምጣት ገቢ ማድረግ አለበት፡፡
9. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ዝርዝር ሰነድ ላይ ስምና አድራሻቸውን በግልጽ በመሙላት በማህተምና ፊርማ ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል።
10. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ያበቃና በጂንካ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 203 በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን በሥራ ቀን ካልዋለ በቀጣዩ የሥራ ቀን ይሆናል።
11. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0467750459, 0468966519 መጠየቅ ይችላሉ
የጂንካ ፖሊ ቴክኒክ ኮሴጅ
