የጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ብ/ክ/መንግሥት ሰሜናዊ ሲዳማ ዞን የወንዶ ገነት ከተማ አስተዳደር በስሩ ለሚገኙ ከተሞች የመሠረተ ልማት መንገድ ጥገና የሚውል፦
* ሴሌክት ማቴሪያል የማቅረብ ሥራ፤
* ሎደርና ዳምፕ ትራከ ማሽነሪ ኪራይ
* ግሬደርና ሮለር ማሽነሪ ኪራይ
* የዶዘር ማሽነሪዎችን ኪራይ በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሠረት፡-
1. የኮንስትራክሽን ማሺነሪ አቅራቢዎች የሆኑ ተጫራቾች ከሥራው ጋር አግባብነት ያለውን ለ2016 ዓ.ም የታደሰ የንግድ /የአገ/ት ሥራ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ ታክስ ክሊራንስ፣ ቫት ተመዝጋቢ፣ እንዲሁም ታክስ ከፋይ መሆኑን የሚገልፅ ማስረጃ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፤
2. የጠጠር መንገድ ግንባታ ሥራ ለማሠራት መ/ቤቱ የሚፈልገውን የማሺን ብዛት በአንድ ፓኬጅ ውስጥ የተገለፀውን ማቅረብ የሚችል፤
3. ተወዳዳሪዎች ለውድድር ያቀረቡት ብቃት/ቴክኒካል/ ማወዳደሪያ ሰነዶች ኦርጅናል ሲጠየቁ አቅርበው ማመሳከር አለባቸው፤
4. የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ /Bid-Bond Security/ በባንክ የተረጋገጠ 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ/ ከቴክኒካል ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ _ ይኖርባቸዋል፤
5. የጨረታ ሰነዱን ቴክኒካል አንድ ኦርጂናልና ሁለት ፎቶ ፋይናንሻል አንድ ኦርጂናልና ሁለት ፎቶ ኮፒዎች ለየብቻቸው በሰም ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተው እና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመጻፍ ህጋዊ የሆነ የድርጅቱ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዱን 300 /ሶስት መቶ ብር/ ወ/ገ/ከ/ ገቢዎች ቅ/ጽ/ቤት ከፍለው ሰነዱን ከወ/ገ/ከ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት መውሰድ ይችላሉ፤
6. የሥራ ተቋራጮች ከጨረታ መመዝገቢያ ቀን በፊት የግንባታ ሳይት በራሳቸው ወጪ ዓይተው ማረጋገጥ አለባቸው፡፡
7. በጨረታ አከፋፈት ስነ ስርዓት የተነበበው ዋጋ እና በአርትሜቲክ ቼክ በሚደረግበት ጊዜ በሁለቱ መካከል 2% በላይም ሆነ በታች በቀጥታ ከጨረታው ውጪ ይደረጋል፡፡
8. የጨረታ ሰነድ ሳጥኑ በ22ኛው ቀን ከቀኑ 3፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን በ3፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ቦታና ሰዓት ይሆናል፤የተጫራቾች ያለመገኘት ጨረታውን መክፈትን አያግደውም።
9. አንድ ተጫራች አንድ ሰነድ ብቻ ለመግዛት ይፈቀዳል ፡፡
10.መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፤
ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 09 16 04 60 74 / 09 16 02 91 50/ ደውለው
መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የወንዶ ገነት ከተማ
አስተዳደር ፋ/ኢ/ስ/ጽ/ቤት
