የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት አደጋ ደርሶባቸው ስደንበኞቹ ሙሱ የመድን ካሣ ከፍሱ የተረከባቸውን፦
▪ ቀረጥ የተከፈለባቸው ልዩ ልዩ ተሽከርካሪዎች
▪ ልዩ ልዩ የተሽከርካሪ ውጫዊና የውስጥ አካላት
▪ የተለያዩ ብረታ ብረቶችን በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ማንኛውም የስም ማዛወሪያ፣ ተጨማሪ የጉምሩክ ቀረጥ፣ ግብር፣ እሴት ታክስና ሌሎች ወጪዎች ቢኖሩ ከፍሎ ለመግዛት
የሚፈልግ ሁሉ ቃሊቲ ክራውን ሆቴል በስተጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ሪከቨሪ ቴከኒክ ማዕከል በመገኘት ግንቦት 7 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 21 ቀን 2016 ድረስ በመመልከትና የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ መድን ድርጅት/Ethiopian Insurance Corporation/ ስም በተሰራ ሲ.ፒ.ኦ በማስያዝ መጫረት ይችላል፡፡
በተጨማሪም የሰሌዳ ቁጥሩ 3-59470 ኢት ሲኖ ገልባጭ ተሽከርከሪ በትግራይ ክልል ካልተ አውላዕሎ ወረዳ ልዩ ስሙ እንደአብርሃ ወአፅበሐ አካባቢ ገደል ውስጥ ተገልብጦ የሚገኝ ሲሆን በመለዋወጫነት በጨረታ ስለሚሸጥ ተጫራቾች በቦታው መመልከት ትችላላቹ
ስበስጠ መረጃ፦ መቐሌ ዲስትሪክት ስልክ ቁጥር:- 0344405275/0911958737 መደወል ይቻላል፡፡
ሀ/ የዕቃ ማስያዣ- የጨረታ መነሻ ዋጋ 20 በመቶ ሲሆን ዝቅተኛ የዕቃ ማስያዣ ብር 1000 ነው፡፡
ለ/ የተሽከርካሪ ማስያዣ
|
የጨረታ መነሻ |
እስክ ብር 50,000.00 |
20 በመቶ |
|
ከብር 50,001.00 |
እስክ ብር 100,000.00 |
ብር 15,000.00 |
|
ከብር 100,1000.00 |
እስክ ብር 200,000.00 |
ብር 25,000.00 |
|
ከብር 200,001.00 |
እስክ ብር 300,00.00 |
ብር 37,000.00 |
|
ከብር 300,001.00 |
እስክ ብር 400,000.00 |
ብር 50,000.00 |
|
ከብር 400,001.00 |
እስክ ብር 500,000.00 |
ብር 60,000.00 |
|
ከብር 500,001.00 |
እስክ ብር 800,000.00 |
ብር 75,000.00 |
|
ከብር 800,001.00 |
ብር በላይ |
ብር 100,000.00 |
ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ በፊት በመሙላት የጨረታውን ሠነድ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ 1ዐ፡ዐዐ ሰዓት ድረስ ለገሀር በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ግንቦት 22 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ቃሊቲ በሚገኘው በሪከቨሪ ቴክኒክ ማዕከል ይከፈታል፡፡ በጨረታው ተሸናፊ ለሚሆኑ ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ከሁለት የሥራ ቀናት በኃላ ተመላሽ የሚደረግ ሲሆን ለአሸናፊዎች ግን ሂሳቡ በገዙት ንብረት ላይ የሚታሰብ ሆኖ የገዙትን ንብረት ተጫራቾች መክፈል ከጀመሩበት ቀን ጀምሮ በ10 ቀናት ጊዜ ውስጥ ከፍያ አጠናቀው ንብረቱን ባይረከቡ ለጨረታ ተሳትፎ ያስያዙት ገንዘብ በመቀጫ መልክ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፡፡ ክፍያ ፈፅመው ንብረቶቹን በተገለፀው ጊዜ የማያነሱ ተጫራቾች የጥበቃ ወጪ በቀን ብር 150 ( አንድ መቶ ሃምሳ ብር) ይከፍላሉ፡፡
ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ያሸነፈውን ተሽከርካሪም ሆነ ቁሳቁስ በአለበት ሁኔታ በአንድ ጊዜ ማንሳት አለበት፡፡ ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ ማብራሪያ፡- በስልክ ቁጥር 011439-25-89 እና 011439-25-45 መጠየቅ ይቻላል፡፡
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት
