ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ የሞጆ ወደብና ተርሚናል ቅ/ጽ/ቤት
የጨረታ መለያ ቁጥር ሞ/ወ/ተ/03/2016
የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ የሞጆ ወደብና ተርሚናል ቅ/ጽ/ቤት ለኤክስፖርት የሚያገለግሉ ባዶ ኮንቴነሮችን ለማስጫን ስለፈለገ የጭነት ትራንስፖርት ማህበራትን በማወዳደር ከአሸናፊው ማህበር ጋር ውል በማሰር ማሰራት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ማህበራትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ሎት ሶስት፡- የባዶ ኮንቴነር ማመላለሻ አገልግሎት ግዥ
በዚህም መሰረት፡-
1. ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ከፍለው ንግድ ፍቃዳቸውን ያሳደሱና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ 100/አንድ መቶ/ ብር በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን በኋላ ባሉት ተከታታይ 10/አስር / የስራ ቀናት ውስጥ ሞጆ ወደብና ተርሚናል ቅ/ፅ/ ቤት በሚገኘው 3ኛ ፎቅ በግዥ እና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 308 በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
3. ከትራንስፖርት ባለስልጣን የተሠጠ የተሽከርካሪዎችን _ ዝርዝር _ ከነ _ ሰሌዳ ቁጥር ወይንም የተሽከርካሪዎቹን የባለቤትነት ደብተር /ሊብሬ/ ዝርዝር ማቅረብ አለባቸው፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ 100/አንድ መቶ/ ብር በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ /no/አስር/ የስራ ቀናት ውስጥ ሞጆ ወደብና ተርሚናል ቅ/ፅ/ ቤት በግዥ እና ንብረት አስተዳደር ቢሮ በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 (አስር ሺህ) ብር በንግድ ባንክ፣ህብረት ባንክና ኦሮሚያ ህ/ስ ባንክ በተረጋገጠ CPO ከጨረታ ሰነዶች ጋር ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
6. . ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ ኦሪጅናል እና ኮፒ በ 2(ሁለት) ፖስታ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀናት በኋላ ባሉት 10(አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
7. አንድ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በወጣ አስረኛው(10) ቀን ላይ ከቀኑ 8፡00ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
9. የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚደርስ ማንኛውም ሰነድ ሳይከፈት ለተጫራቹ ይመለሳል፡፡
10. በተጫራቾች የሚሞላ ዋጋ ስርዝ ድልዝ የሌለው እና በግልፅ የሚታይ መሆን አለበት፡፡
11. ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- በስልክ ቁጥር 0221162194 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ የሞጆ ወደብና
ተርሚናል ቅ/ጽ/ቤት
