Tender Detail

Tender Details

  • Company Commercial Bank of Ethiopia (የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-551-50-04
  • Websitehttps://combanketh.et/
  • Deadline14 May 2024, 5:05 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Organizational

የጨረታ ማስታወቂያ

Commercial Bank of Ethiopia (የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)


በድጋሚ የወጣ የተስያዩ ያገስገሱ ንብረቶች ጨረታ ቁጥር 003/2023/24 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያገለገሉ የተለያዩ ፈርኒቸር ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

1. ስለ አሻሻጡ የተዘጋጀውን ዝርዝር ሁኔታ የያዘውን ሰነድ ቄራ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ሕንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 21 የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ከሚያዝያ 29 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ግንቦት 12 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ባሉት የሥራ ቀናት መውሰድ ይችላሉ፡፡

2. ተጫራቾች ያገለገሉ ንብረቶችን ከሚያዝያ 29 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 13 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቃሊቲ ቅርንጫፍ ትይዩ ባለው አስፓልት ወደ ውስጥ ገባ ብሎ በሚገኘው የቀድሞ ብራሌ ጥጥ መዳመጫ ግቢ እና ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፊት ለፊት ዛጉዌ ሕንፃ ግራውንድ ውስጥ ከጠዋቱ ከ2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ባሉት የሥራ ቀናት በመገኘት ማየት ይችላል፡፡

3. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ላገለገሉ የንብረት ዓይነቶች የጨረታ የመነሻ ዋጋውን 25% (ሃያ አምስት በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) በባንከ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለያገለገሉ ንብረቶች አስወጋጅ (Commercial Bank of Ethiopia Disposal) በሚል ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

4. የተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥን ግንቦት 14 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ላይ ታዛቢዎች በተገኙበት ይታሸጋል፡፡

5. ተጫራች ለንብረቱ የሚሰጠውን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ባለው ክፍት ቦታ በመሙላት የጨረታ ማስከበሪያ እና ሌሎችም አስፈላጊ ሰነዶችን በፖስታ በማሸግ ቄራ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሕንፃ 2ኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ ግንቦት 14 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት እስከ 4፡00 ሰዓት ብቻ ያስገባል፡፡

6. ግንቦት 14 ቀን 2016 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም ታዛቢዎች በተገኙበት ቄራ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሠራተኞች የመዝናኛ ክበብ አዳራሽ በግልጽ ይከፈታል፡፡

7. ለጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ የተያዘው ገንዘብ አሸናፊ ለሚሆነው በሚገዛው ንብረት ክፍል ላይ የሚታሰብ ሲሆን አሸናፊ ላልሆኑት ለጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ያስያዙት ገንዘብ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡

ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀነው፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

Save Tender