የጨረታ ማስታወቂያ የግዥ መለያ ቁጥር DDFTZ/NCB/G/01/2016
በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የድሬደዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የድሬደዋ ነፃ ንግድ ቀጠና የተለያዩ የኤሌክትሪካል ፤ የግንባታ እና የሳኒተሪ እቃዎችን በሀገር ውስጥ ግልጽ ጨረታ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
1. በጨረታው መሳተፍ የሚችሉት በዘርፉ የተሰማሩ እና የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ ህጋዊ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ /ፐIN/ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ከሆኑ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው ፡፡
2. ተጫራቾች የጨረታ ቴክኒካል ሰነድ ኦሪጂናል እና ኮፒ እንዲሁም ፋይናንሻል ሰነድ ኦሪጂናል እና ኮፒ በተለያየ ኤንቨሎፕ በማሸግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
3. የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል በነፃ ንግድ ቀጠናው የአንድ ማዕከል አገልግሎት አስተዳደር ቢሮ ሁለተኛ ፎቅ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ። የቅርንጫፉ የሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡30 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከ 7፡30 እስከ 10፡30 እንዲሁም ቅዳሜ ከ 2፡30 እስከ 6፡00 በመምጣት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
4. የጨረታ ማስከበሪያ በአንድ ሎት 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ብር በCPO ወይም ሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በእለቱ በ 4፡45 ላይ በስብሰባ አዳራሽ ıኛ ፎቅ ይከፈታል።
6. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡-
በድሬዳዋ ከተማ ገደንሰር ቀበሴ የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና
የአንድ ማዕከል ሕንፃ ፣2ኛ ፎቅ ቢሮ ፋይናንስ እና አስተዳደር ቢሮ ፣
ስልክ:- 0921875123/0929063731
በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የድሬደዋ
ኢንዱስትሪ ፓርክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
