የቁም ደን ሽያጭ ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር OFWE I/A/B/GU/2016
በኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት የኢሉባቦር ቅ/ጽ/ቤት
የኦሮሚያ ደንና ዱር እንሣት ድርጅት በኢሉባቦር ደንና ዱር እንሣስት ቅ/ጽ/ቤት ስር ገባዲደሳ ድስትሪክት ስር የሚያስተዳድሩትን የቁም ባህርዛፍ በጨረታ አወዳድሮ መሽጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም፦
- የጊድላ፤ የአጣና፣የእንጨት መሰንጠቂያ እና ተዛማጅ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ድርጅቶች እና ግለሰቦች እንዲሁም የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ስለ ጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚግልፅ የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዳቸው 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በኢሉባቦር ቅ/ጽ/ቤት መቱ ቶታል ማደያ ፊት ለፊት በሚገኘው ፎቅ ግራዎንድ(Ground) ቢሮ ቁጥር 02 በመግዛት በጨረታው መሣተፍ ይችላሉ።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ/የወጣበት ቀን ጨምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣው ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆያል።
- ጨረታው የሚዘጋበት እና የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት በጨረታው ሰነድ ውስጥ ይገለጻል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid bond) የሚሆን ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 5% በማስላት በባንክ በተረጋገጠ ደረሰኝ (CPO) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፦ በስልክ ቁጥር 0474414196 መደወል ይችላሉ
በኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት
የኢሉባቦር ቅ/ጽ/ቤት
