Tender Detail

Tender Details

  • Company ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ
  • Address , Phone: 058-555-80-32
  • Website
  • Deadline08 May 2024, 4:50 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Organizational

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ


የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ለ2016 በጀት ዓመት ለዩኒቨርስቲው አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎች 1ኛ ደንብ ልብስ፣ 2ኛ የተለያዩ ለምግብ ቤት አገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሪከ እቃዎች እና መለዋወጫዎች፣ 3ኛ የአይሲቲ ዕቃዎች፣ 4ኛ የተለያዩ የበር ቁልፍ፣ 5ኛ የመኪና ጎማ፣ 6ኛ ለጄነሬተር አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች፣ 7ኛ የጽዳት እቃዎች፣ 8ኛ የውሃ እቃ፣ 9ኛ የምግብ ግብዓት፣ 10ኛ ለህጻናት ማቆያ የሚያገለግሉ የተለያዩ እቃዎች በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ማስያዝ ያለባቸው የጨረታ ማስከበሪያ:- 1ኛ ደንብ ልብስ ብር 100,000.00፤ 2ኛ የተለያዩ ለምግብ ቤት አገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሪክ እቃዎች እና መለዋወጫዎች ብር 100,000.00፤ 3ኛ የአይሲቲ ዕቃዎች ብር 100,000.00፤ 4ኛ. የተለያዩ የበር ቁልፍ ብር 100,000.00፤ 5ኛ የመኪና ጎማ ብር 100,000.00፤ 6ኛ ለጀነሬተር አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች እና መለዋወጫዎች ብር 100,000.00፤ 7ኛ የጽዳት እቃዎች ብር 50,000.00፤ 8ኛ የውሃ እቃ 100,000፤ 9ኛ የምግብ ግብዓት ብር 100,000.00፤ 10ኛ ለህጻናት ማቆያ የሚያገለግሉ የተለያዩ እቃዎች ብር 50,000.00 የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን

1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፤

3. ከግዥ እና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት በድረ-ገጽ /egp/ የተመዘገቡ!

4. የግዢ መጠን ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት የታከስ ከፋይነት ሰርተፊኬት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤

5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቀ 1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች የኦሪጅናል ፎቶ ኮፒ ከመጫርቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፤

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ደባርቅ ዩኒቨርስቲ ግዢ ቢሮ ወይም አዲስ አበባ ካለው 22 አዲሱ መሬት አስተዳደር ጀርባ ጊዜያዊ ቢሯችን በመምጣት የማይመለስ 150 ብር /አንድ መቶ ሀምሳ ብር/ ብቻ በመግዛት መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

7. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከባንከ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ

ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና፤በጥሬ ገንዘብ (በመሂ 1) ለ120 ቀናት እና ከዚያ በላይ ዋስትና በማሰራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር በጥንቃቄ በማሸግ ከዚህ በላይ የተጠቀሰውን ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡

8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ደባርቅ ዩኒቨርስቲ ግዥ ቢሮ በተዘጋጀው ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት የሚገባ ሆኖ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማለትም በ20/08/2016 ዓ.ም አንስቶ እስከ 15 ኛው ተከታታይ ቀን 11፡30 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱ የሚሸጥ ይሆናል፡፡

9. ሁሉም ጨረታዎች ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ግዥ ቢሮ ጨረታው በወጣ ማለትም አዲስ አበባ የተሸጠው ሰነድ እስከ ደባርቅ ዩኒቨርሊቲ እስኪመጣ ድረስ ተጠብቆ በ19ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ታሽጎ በዚያው ቀን 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ይሁን እንጂ የጨረታ ኮሚቴው ባይሟላ እና ብሄራዊ በዓል ወይም እሁድና ቅዳሜ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተባለው ሰዓት ታሽጎ በተባለው ሰዓት ይከፈታል፡፡

10. የወሰዱትን የጨረታ ሰነድ በእያንዳንዱ ገጽ በመፈረም የድርጅቱን ማህተም እና አድራሻ አድርጎ መመለስ አለባቸው፡፡

11. ሰነዱ ሲሞላ ስርዝ ድልዝ እንዳይኖር ጥንቃቄ መደረግ ይገባዋል፡፡ ካለም ሰነዱን በሞላው አካል በፊርማ መረጋገጥ ይኖርበታል፤ ይህ ካልሆነ ግን ሰነዱ ተቀባይነት አይኖረውም፤ እንዲሁም ሰነዱ የተሟላ መሆኑን ሲገቡ ቆጥረው መረከብና ሞልተው ሲመልሱም የተሞላውንም ሆነ ያልተሞላውን ሰነድ እንደተሟላ መመለስ ግዴታ ሲሆን ሰነዱን ያጎደለ ተጫራች በራሱ ፍላጎት ከጨረታው እንደተሰረዘ ይቆጠራል፡፡

12. ተጫራቾች ለግዥ መመሪያው ተገዥ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡

13. ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

14. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ማብራሪያ ካፈለገ የጨረታ ሰነድ ማስረከቢያ ቀነ ገደብ ሊያልቅ 5 ቀን ከመቅረቱ በፊት ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ግዥ ቢሮ ወይም አዲስ አበባ ካለው 22 አዲሱ መሬት አስተዳደር ጀርባ ጊዜያዊ ቢሯችን ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058-555-80-32/ 09-18-73-10-31 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ

Save Tender