Tender Detail

Tender Details

  • Company በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በደቡብ ኦሞ ዞን የኛንጋቶም ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት
  • Address , Phone: 91 616 0758
  • Website
  • Deadline22 May 2024, 1:46 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Organizational

የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በደቡብ ኦሞ ዞን የኛንጋቶም ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት


በደ/ብ/ብ/ከ/መ የኛንጋቶም ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት በ2016 በጀት ዓመት በተመደበ በጀት ለሆስቴል ተማሪዎች ቀለብ የሚሆን እህልና የእህል ማጣፈጫዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በዚህ መሰረት በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን በማሟላት በጨረታ መወዳደር ይችላል።

♦ በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው

♦ የዘመኑን ግብር የከፈሱና ፈቃዳቸውን ያሳደሱ

♦ የግብር ከፋይነት መስያ ቁጥር ያላቸው

♦ የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ ተመዝጋቢ የሆኑ

♦ የአቅራቢዎች ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው

 ከላይ የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የሚያሟሉ አቅራቢዎች ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15/አሥራ አምስት/ ቀናት ብቻ በ100/አንድ መቶ ብር/ የዕቃውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ በኛ/ወ/ፋ/ጽ/ቤት ማግኘት ይችላሉ። ተጫራቾች በአሥራ ስድስተኛዉ ቀን ከረፋዱ 3፡30 ሰዓት ላይ ሠነዱን በታሸገ ኢንቨሎኘ ዋናውንና አንድ ኮፒ (አንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ) በማድረግ ከደ/አ/ዞ/ኛ/ወ/4/ጽ/ቤት ቢሮ ለዚሁ ተግባር ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅበታል። ጨረታው በዚሁ በእለቱ ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፣ በአሥራ ስድስተኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፣

ማሳሰቢያ

  • መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  • ጨረታው በሚከፈትበት እለት ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 10,000/ አሥር ሽህ ብር/CPO/ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፣
  • በጨረታ መክፈቻ ወቀት የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታ ሂደቱን እያስተጓጉልም።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት

በደቡብ ኦሞ ዞን የኛንጋቶም ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት

Save Tender