Tender Detail

Tender Details

  • Deadline18 Apr 2024, 5:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Organizational

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 06/2016


የጨረታ አይነት

ሎት፡-1 ሱፐር ማርኬት

አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በ2016 በጀት ዓመት በሎት 1 እና በሎት 2 ላይ የተገለጹትን ሱቆች መስፈርቱን አሟልተው ለሚገኙ ድርጅቶች ማከራየት ይፈልጋል፡

1. በዘርፍ ህጋዊ ፍቃድ ያለውና የ2015ዓ.ም የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸው፡፡

2. የጨረታ ማስረከቢያ ብር 50,000/ሃምሳ ሺህ ብር/ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ከፍያ ማዘዣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ስም cpo (ጋራንቲ ቦንድ) በማሰራት ማስያዝ ::

3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ የሚቆይ ጊዜ ከመጨረሻው ቀን በኋላ ለተጨማሪ 28 ቀናት ፀንቶ ይቆያል።

4. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ 500 (አምስት መቶ ብር) በመከፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሀሳቦችን የአንዱን ካሬ ዋጋ እና ጠቅላላ ካሬ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን ያካተተ ዋጋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው ቢሮው በሰጣችሁ ፎርማት ላይ በመሙላት እና የድርጅታችሁን ማህተም ፊርማና ሙሉ አድራሻችሁን በመግለጽ፤-

6.1 ፋይናንሻል አንድ ኦርጅናል እና ፋይናንሻል አንድ ኮፒ

6.2 ቴከኒካል አንድ ኦርጅናል እና ቴክኒካል አንድ ኮፒ በማድረግ በሰም በታሸገ በተለያዩ ፖስታዎች ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

7. የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከሰኞ- ዓርብ ከ2፡30-11፡00 ሰዓት ድረስ የግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 401 በዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

8. የጨረታ ማስታወቂያ በወጣ በከኛው ቀን ማለትም የሥራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያኑ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

9.ማንኛውም ተጫራች በሌሎች ተጫራቾች ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት (ማቅረብ) አይቻልም፡፡

10. ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011 8 12 61 79 /011 1 70 30 24 / በመደወል መረጃ መጠየቅ ይቻላል፡፡

ድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ፒያሳ አራዳ ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 401

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ

Save Tender