Tender Detail

Tender Details

  • Company የካፋ ማህበረሰብ ቴሌቪዥን ጣቢያ
  • Address , Phone: 0924 81 30 22
  • Website
  • Deadline22 Apr 2024, 4:43 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Organizational

የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር፡- የግ/m/ቁጥር 01/2016

የካፋ ማህበረሰብ ቴሌቪዥን ጣቢያ


የካፋ ማህበረሰብ ቴሌቪዥን ጣቢያ በ2016 በጀት ዓመት ለቴሌቪዥን ጣቢያው አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የሚዲያ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ተጫራቶችን በመጋበዝ ለመግዛት እንደሚከተለው በሎት በመከፋፈል እስከ በጀት ዓመቱ ማብቂያ ማለትም እስከ ሰኔ 30/2016 ዓ.ም ድረስ

ሎት 1 ድሮን ካሜራ

ሎት 2 የተለያዩ ኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎች የቪዲዮ ካሜራን ጨምሮ

ሎት 3. ባለ 3 እግር ተሽከርካሪ /ባጃጅ)

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራች

*በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የንግድ ምዘገባ የአቅራቢነት ሰርተፍኬት ፣ የቲን /TIN/ እና ቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።

*ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች የጨረታ ዶክመንት ሊገዙ ሲመጡ ኦሪጂናሉን እና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ አቅርበው እንዲመሳከር የማድረግ ግዴታ አለባቸው።

በመሆኑም ተጫራቾች ለሁሉም ሎቶች ለእያንዳንዳቸው የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 300.00 /ሶስት መቶ ብር / የካፋ ማህበረሰብ ቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርበዉ በመከፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ለተከታታይ 15 ቀናት የካፋ ማህበረሰብ ቴሌቪዥን ጣቢያ ግዥ ንብ/አስ/ሥራ ሂደት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

*ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ

ሎት 1. ድሮን ካሜራ ብር 80,000 /ሰማኒያ ሺህ ብር/ሎት 2 የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችና ቪዲዮ ካሜራን

ጨምሮ ብር 80,000 /ሰማኒያ ሺህ ብር/

ሎት 3. ባለ 3 እግር ተሽከርካሪ /ባጃጅ/ ብር 80,000 /ሰማኒያ ሺህ ብር/ በካፋ ማህበረሰብ ቴሌቪዥን ግዥ ንብ/አስ/ሥም በማሰራት ከኦሪጂናል ቴከኒካል ጨረታዉ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፡፡

  • ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በየሎት በመከፋፈል እና የሎት ቁጥሩን ሠነዱ ላይ በመፃፍ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ፋይናንሻልና እና ቴክኒካል የጨረታ ዶከመንት ተገቢውን ፊርማ እና ማህተም በማሳረፍ ለየብቻ አንዳንድ ኦሪጂናል የተሟላ ሰነድ በሰም /በሙጫ በታሸጉ ፖስታዎች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በካፋ ማህበረሰብ ቴሌቪዥን ጣቢያ ግዥ ንብ/አስ/በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  • የጨረታው ሳጥን በ16ኛው ቀን በ3፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 3፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በካፋ ማህበረሰብ ቴሌቪዥን ጣቢያ ይከፈታል፡፡ የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል። በመክፈቻው እለት የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮች ያለመገኘት የጨረታ መክፈት ሂደት እያስተጓጉልም፡፡

ተጫራቶች አሰሪው መ/ቤት ያዘጋጀውን የቴከኒካል ዶክመንት መጠይቅ ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

* አሸናፊው ማሸነፉ ሲረጋገጥ ያሸነፈበትን የጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ /Performance Bond/

 ለማስያዝ ፈታደኛ መሆን አለበት ፡፡

* አሸናፊው ማሸነፉ ከተገለፀበት ጀምሮ 7/ሰባት/ የሥራ ቀናት በኋላ በቴሌቪዥን በጣቢያው በመገኘት ውል መግባት አለበት፡፡

* አሸናፊው ድርጅት ከላይ በሎት የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በሙሉ በራሱ ወጪ የካፋ ማህበረሰብ ቴሌቪዥን ጣቢያ

አቅርቦ የማስረከብ ግዴታ አለበት፡፡

*ቴሌቪዥን ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::

ለተጨማሪ መረጃ- በቢሮ ለውጥ ምክንያት መደበኛው ስልክ ቁጥር 047 331 17 12 ባለመስራቱ በሞባይል ቁጥር:- 0925 26 39 13 /0924 81 30 22 በመደወል መጠየቅ ይቻላሉ፡፡

የካፋ ማህበረሰብ ቴሌቪዥን ጣቢያ

Save Tender