Tender Detail

Tender Details

  • Deadline21 Apr 2024, 6:20 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Organizational

ሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ለአገልግሎት የማይጠቀምባቸው የተለያዩ ኤሲና ፍሪጅ እንዲሁም አነስተኛ ጀኔሬተር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ


የጨረታ ቁጥር

የጨረታው ሰንድ ሽያጭ የሚጀምርበት ቀን

የጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት

የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት

CCSE-Branch

/004/2016

ሚያዝያ 8/2016

ሚያዝያ 21/2016

ከቀኑ 4፡00

ሚያዝያ 21/2016 ከቀኑ 4፡30

በኢፌዴሪ ጉምሩክ ኮሚሽን የሰመራ ጉ/ቅ/ቤት ለአገልግሎት የማይጠቀምባቸው ኤሲና ፍሪጅ እንዲሁም አነስተኛ ጀኔሬተር በግልጽ ጨረታ ሽያጭ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም ድርጅት ወይም ግለሰብ ተጫራች

ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማJላት ቀርቦ መወዳደር ይችላል።

1 በጨረታ ሽያጭ ስርዓት ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራች በዘርፉ የጸና የታደሰ ንግድ ፍቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ

2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ ከጠዋት 1፡00-6፡00 እና ከሰዓት 9:00-12፡00 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋት 1፡00- 5፡00 የማይመለስ ብር 100.00(አንድ መቶ) ብር በመክፈል በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በመሃኘት ይህ ጨረታ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በግዥና ፋይናንስ ቢሮ በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይቻላል፡፡

3. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና CPO በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት (ETHOPIAN CUSTOMS COMMISSION SEMERA BRANCH OFFICE) ስም በባንክ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

4. ጨረታው ከሚያዝያ 8/08/2016 እስከ ሚያዝያ 21/08/2016 ዓ.ም ተከታታይ ለ15 ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ይሆናል፡፡

5. ጨረታ የሚካሄድበት ቦታ በሠመራ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በሀብት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ሲሆን ጨረታው ሚያዝያ 21/08/2016 ከጧቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

6. የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 20/08/2016 9.90 ዓ/ም

7. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ተመላሽ የሚደረገው ላሸነፈበት ዕቃ ሙሉ ክፍያ ከፈጸመ እና የተከፈለበት ዕቃ ሙሉ በሙሉ ማንሳቱ ከተረጋገጠ በኋላ ነው :: እንዲሁም ለተሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ውጤት በተገለጸ በሦስት (3) ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡

8 አሸናፊው ተጫራች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በአምስት (5) ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትንት እቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ያለበት ሲሆን ይህንን ባይፈጽም ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ውዝስትና ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ሆኖ ናል። ሆኖም እቃውን ከ1ወር በላይ ከቆየ ለንብረቱ የከፈለው ዋጋ ለመስሪያቤቱ ገቢ ሆኖ እቃው እንደተተወ ተቆጥሮ በሽያጭ ይወገዳል።

9 መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይንም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10 ተጫራቾቹ ተመሳሳይ የዕቃ ጠቅላላ ድምር ቢያቀርቡ ቃለ ጉባኤ በመያዝ በአጣ የምንሰይ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

11 ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነድ የተሰጠውን ዋጋ መለወጥ ማሻሻል ወይም ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይቻልም፡፡

12. አሸናፊው የሚለየው በጠቅላላ ድምር ስለሆነ የእያንዳንዱ እቃ ዋጋ ዝርዝር መሞላት አለበት

13 በጨረታ ለሚሸጥ ዕቃ የጨረታው ውጤት በደብዳቤ እንደተገለጸ ከአሸናፊው፡፡ የሽያጭ ውል እንደተደረገ ይቆጠራል።

14 አሸናፊው ተጫራች ዕቃዎቹን ባሉበት ሁኔታ በመረከብ፣ ለመረከብ እና ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሁሉ ራሱ ይችላል፡፡

15.ቅ/ጽ/ቤቱ ለጨረታ የቀረበውን እቃ ብዛት ለመጨመርም ሆነ ለመቀነስ ሙሉ መብት አለው፡፡

16.ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃዳቸውን እና ለእያንዳንዱ ዕቃ የሚገዙበትን ዋጋ ቫትን (VAT) ጨምረው በዋጋ ማስገቢያ ቅጽ ላይ በመሙላት እና የጨረታ ማስከበሪያ ሰነዱን (CPO) በማካተት በታሸገ ኤንቨሎፕ ሙሉ አድራሻቸውን እና የጨረታ ቁጥሩን በመጥቀስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን እስከ ሚያዝያ 21 ቀን 2016 ዓ.ም ጠዋት ከ4፡00 ሰዓት በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ስ.ቁ-0333661567/0921121359/0914362075

በኢፌዴሪ ጉምሩክ ኮሚሽን የሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት

Save Tender