ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር:- 02/2016
በአብክመ ደቡብ ወሎ ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር መምሪያ የወረኢሉ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት
በአብክመ ደቡብ ወሎ ዞን የወረኢሉ ከተማ አስ/ር ከ/ጽ/ቤት ለጀመረው G.4 ህንጻ የጣራ ስራ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት የግንባታ ደረጃቸው ጂሊ/ቢ ሲ 6 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የሚከተለውን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫሪቶችን እንዲጫረቱ ይጋብዛል፡፡
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
2 የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN NO/ ያላቸው
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተጠቃሚ የሆኑ፤
4. የገቢዎች ከሊራንስ እስከ 3 ወር የከፈለበትን መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 2 % በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ፣ ቼክ፣ በከ/አስ/ግ/ጽ/ቤት በካሽ በማስያዝ ከሰነዱ ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
6 አጠራጣሪ መረጃዎች ቀርበዋል ተብሎ ሲታመንበት ኦሪጅናል መረጃዎችን ማቅረብ የሚችሉ፡፡
7. ጨረታው በሚከፈትበት ዕለት ኦሪጂናል የብቃት ማረጋገጫ፣ የንግድ ፈቃድ፣ የምዝገባ ምስከር ወረቀት፤ የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት፣ የቲን ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት መረጃዎችን ይዘው የሚገኙ፡፡
8. የሚፈለገውን የስራ ዝርዝር ከሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
9. ተጫራቶች ከአሁን ቀደም በያዟቸው ፕሮጀከት ላይ ማጓተት እና ማጉላላት በመፍጠራቸው ማስጠንቀቂያ / ቅጣት/ ያልተላለፈባቸው ለመሆኑ መረጃ ከአሰሪው መ/ቤትም ሆነ ከከተማ መሰረተ ልማት መምሪያ /ቢሮ/ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
10. የዋጋ ማቅረቢያውን ሰነድ (Financial document) በh/አስ/ገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 በመገኘት ማስታወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 21 ቀናት ውስጥ በስራ ሰዓት የተቀመጠውን የገዥ አድራሻ እና የስራ ሁኔታ በመሙላት ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
11. ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተገለጹትን በማሟላት የጨረታ ሃሳባቸውን በአንድ ፖስታ ውስጥ ሁለት ፖስታ በማድረግ ኦሪጅናል፣ ኮፒ በማለት ወይም በሁለት ፖስታ ዋና እና ቅጅ በማለት በተለያየ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸማ በከተማ አስተዳደሩ ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስታወቂያው እየር ላይ ከዋለበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 21 ቀናት ውስጥ በስራ ሰዓት እየተገኙ ማስገባት ይችላሉ፡፡
12. ጨረታው ማስታወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ዕለት ጀምሮ በሚውለው 22ኛ ቀን ከጠዋቱ 3:30 ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
13. በጨረታ ሰነዱም ሆነ በፖስታዎቹ ላይ የድርጅቱ ፊርማ እና ማህተም መኖር አለበት፡፡
14. ምንም አይነት ስርዝ ከጨረታ ውጭ ያደርጋል፡፡
15. አሸናፊ ተቋራጭ አሸናፊነቱ ከተገለጸበት እለት ጀምሮ ካሉት 5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የመልካም አፈጻጸም ዋስትና ከባንክ /ኢንሹራንስ/ በማስያዝ የስራ መርሃግብር፣ የሰው ሃይል አጠቃቀም የሚያሳይ መርሃ ግብር በማቅረብ ከአሰሪ መ/ቤቱ ጋር ውል መውሰድ ይጠበቅባቸዋል፡፡
16. ውክልና በተመለከተ አቻ እና ከዚያ በላይ ካልሆነ በስተቀር ተጫራቾች ስራውን መስራት የማይችሉ ሲሆን
ወኪሎች በውከልናቸው ላይ ስራውን መስራት እንደሚችሉ መጠቀስ የለበትም፡፡
ማሳሰቢያ: መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
-የጨረታ መክፈቻ ዕለት የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
በአብክመ ደቡብ ወሎ ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር መምሪያ
የወረኢስ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት
