የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 001/2016 ዓ.ም
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የምስራቅ ጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ ቡታጅራ አጠቃላይ ሆስፒታል
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ የቡታጅራ አጠቃላይ ሆስፒታል አገልግሎት የሚውሉ
"ሎት እንድ የፅዳት እቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ የኤሌክትሮኒክ እቃዎች የህንፃ መሳሪያዎችና የውሃ እቃዎች
- ሎት ሁለት x-ray Mashin Ditecter
- “ሎት ሶስት የላብራቶሪ ሪኤጀንት በዚህ መሰረት
1ኛ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መሌ ቁጥር (TIN NUMBER) ያላቸውና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እንዲሁም የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
2ኛ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10.000 (አስር ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ የከፍያ ትዕዛዝ (CPO) ለቡታጅራ አጠቃላይ ሆስፒታል ብለው ማሰራት አለባቸው ወይም ጥሬ ገንዘብ በእያንዳንዱ ሎት ማስያዝ አለባቸው።
3ኛ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ በተራ ቁጥር 1 የተዘረዘረሩትን እና ሌሎች የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያየዘው ማቅረብ አለባቸው።
4ኛ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ በአንድ ሎት አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ፖስታዎች ኦርጂናል እና ኮፒ በመለየት በጥንቃቄ በሰም በታሸገ ፖስታ ቡታጅራ አጠቃላይ ሆስፒታል ግዥ ፋይናንስ ንብረት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ ይችላሉ።
5ኛ የጨረታው ሳጥን የሚታሸገው በ10ኛው ቀን 8:00 ሰዓት ሲሆን በዛው ቀን በ8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቡታጅራ አጠቃላይ ሆስፒታል አጠቃላይ ግ/ፋ/ን/አስ/ ደ/ስ ሂደት ቁጥር 55 በይፋ ይከፈታል።
6ኛ የጨረታው ሳጥኑ የሚታሸግበትም ሆነ የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው የሚከፈተው በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል።
7ኛ ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ አንድ ሎት ብር 100 (አንድ መቶ) በመከፈል ቡታጅራ አጠቃላይ ሆስፒታል ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/ስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 55 ዳይሬከቶሬት የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በio (አስር) ቀናት ውስጥ ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
8ኛ የሚገዙ ዕቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይቻላል።
9ኛ ተጫራቾች ያሸነፉትን ዕቃ በሙሉ በራሳቸው ወጪ ቡታጅራ አጠቃላይ ሆስፒታል ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለባቸው።
10ኛ ሆ/ሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0461151172 ወይም 0461150098 መደወል ደቻላል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የምስራቅ ጉራጌ ዞን
ጤና መምሪያ ቡታጅራ አጠቃላይ ሆስፒታል
