Tender Detail

Tender Details

  • Deadline04 Apr 2024, 12:57 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Organizational

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ መለያ ቁጥር ESLSE/P&T/REQ/2022/23527


የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲከስ የሞጆ ወደብ እና ተርሚናል ቅ/ጽ/ ቤት ለ2016 በጀት አመት የሰራተኞች የሴፍቲ እና የደንብ አልባሳትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት- አምስት፡-የተለያዩ የሴፍቲ እና የደንብ አልባሳት

በዚህም መሰረት፡-

1. በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የቫት የምስከር ወረቀት፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው የሚያሳይ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2. በመንግስት ግዥ እና ንብረት ማስወገድ አገልገሎት ድረ ገፅ (website) ላይ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆኑን የሚያሳይ (supplier list) የምስክር ወረቀት፤

3. የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚያሳይ ስልጣን ካለው አካል የተሰጠ (Valid Tax Clearance)!

4. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ሞልቶ የሚመልሰው በድርጅቱ ድረ- ገጽ (WWW.ESLSE.COM) ላይ በዋና መ/ቤት ምዝገባ ካካሄዱ በኋላ ብቻ በሚሰጣቸው መለያ ቁጥር መሰረት የሚሞሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

5. የጨረታው መከፈቻ እና መዝጊያ ጊዜ ሲስተሙ ላይ በሚወጣው ሰዓት ይሆናል፡፡

6, የጨረታ ናሙና እና ሲ.ፒ.ኦ (50,000 ብር) ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት በቅርንጫፉ ጽ/ቤት የሚገባ ይሆናል፡፡

7. ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- በስልከ ቁጥር 0221162194/0221162181 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ የሞጆ ወደብና ተርሚናል ቅ/ጽ/ቤት

Save Tender