Tender Detail

Tender Details

  • Company Ministry of Innovation and Technology (የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር)
  • Address Lisie G/Mariam, Arada Sub-City, Addis Ababa, Ethiopia, Phone: 09-11-82-52-99
  • Websitehttp://www.mint.gov.et/
  • Deadline19 Apr 2024, 2:45 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Organizational

የጨረታ ማስታወቂያ

Ministry of Innovation and Technology (የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር)


ያገለገሉ የመኪና ጎማና መለዋወጫዎችን በግልጽ ጨረታ ለመሸጥ የተዘጋጀ የጨረታ ሠነደ ቁጥር MInT/PDC/03/2016

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገለገሉ የመኪና ጎማና መለዋወጫዎች ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማJላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

1 በጨረታው የሚወዳደሩት  ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆኖ ሠነድ ለመግዛት ሲመጡ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ ወይም መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

2 ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሊሴ ገ/ማሪያም ት/ቤት ወይም የቀድመው ኦርማ ገራዥ ጀርባ በሚገኘው ህንፃ 3ኛ ፎቅ የመሰረታዊ አገልግሎት ስራ አስፈፃሚ በመምጣት የንብረቶችን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በኢኖቬሸንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተከፈተ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000263705916 ከፍለው መውሰድ ይችላሉ።

3 ተጫራቾች ሰነድ ገንዘብ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ያገለገሉ የመኪና ጎማና መለዋወጫዎች ከላይ በተጠቀሰው መ/ቤት በመሄድ መመልከት ይቻላA:

4. ተጫራቶች የሚገዙትን ያገለገሉ የመኪና ጎማና መለዋወጫዎች የጨረታ መነሻ ዋጋ 10 በመቶ (10%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በታሽ” ኤንቨሎፕ በማድረግ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ህንፃ 3ተኛ ፎቅ የመሠረታዊ አገልግሎት ስራ አስፈፃሚ ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት የኖርባቸዋል።

5  የጨረታ ሳጥኑ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም የመከፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡ እንዲሁም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፡፡

6. በጨረታው አሸናፈ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፈነታቸው በተገለፀላቸው ከ 7 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መከፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ከፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል፡፡

7. የጨረታው መገምገሚያ መስፈርት ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ነው፡፡

8 ያገለገሉ የመኪና ጎማና መለዋወጫዎችን የመነሻ ዋጋ 10 በመቶ (10%) ያልያስያዘ እና በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል፡፡

9. የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡

10. ሚኒስትር መ/ቤቱ ባወጣው ጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድር ውድቅ ይደረጋል፡፡

11. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ንብረቶች ሙሉ ክፍያ ከፍሎ እስከሚወስድ ድርስ ለውል ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን የጠቅላላ ዋጋውን 10 በመቶ በጥሬ ገንዝብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒአ ማስያዝ አለበት፡፡

112. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመከፈል ንብረቶቹን በ10 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡

13. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልከ ቁጥር 09-11-82-52-99 ወይም 09-02-48-36-53 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

14. ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማናቸውም ጊዜ ጨረታውን ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር

Save Tender