የጨረታ ማስታወቂያ የሀገር ውስጥ ግልጽ ጨረታ ቁጥር ሙሲሩ/72/2016
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙግር ሲሚንቶ ፋብሪካ ለፋብሪካ አገልግሎት የሚውል የዲዝል ጄኔሬተር ጥገና የባለሙያ ግዥ በሀገር ውስጥ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
|
S/NO |
Type |
Qty |
|
1 |
SKL Diesel Generator (Heavy Engineering) KARL LIEBKNECHT German) |
1 |
|
2 |
SKL Diesel Generator (Heavy Engineering) KARL LIEBKNECHT German) |
1 |
|
3 |
ENGGA Diesel Generator (China) |
1 |
ስለዚህ ተጫራቾች ሕጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ የተጠቀሱትን ሰነድ በመያዝ የማይመለስ ብር 115.00 /አንድ መቶ አሥራ አምስት ብር/ ከነቫቱ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ በተለምዶ በቅሎ ቤት አካባቢ ጋራድ ሕንፃ ቢሮ ቁጥር 432-3-8 ከሚገኘው የግዥ መምሪያ ቢሮ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች ለጨረታ ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ ብር 2% ጠቅላላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙግር ሲሚንቶ ፋብሪካ ስም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (C.P.O) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባንከ ጋራንቲ ከቴከኒከ ዶከመንቶቹ ጋር በማያያዝ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 6 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ሰነዳቸውን አዲስ አበባ በሚኘገው በግዥ መምሪያ ቢሮ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዕለቱ ግንቦት 6 ቀን 2016 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት በግዥ መምሪያ ቢሮ ይከፈታል፡፡
ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር፡- 0114420216
ፋክስ 0114420688
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን
ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ_
