Tender Detail

Tender Details

  • Deadline18 Apr 2024, 1:49 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Organizational

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


በፍ/ባለመብት ወ/ሮ ጽዮን ዜና ገ/ማርያም እና በፍ/ባለዕዳ አቶ አለምሰገድ ወርቁ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል መጀመሪያ ፍ/ቤት በመ/ ቁጥር 125156 ግንቦት 24 ቀን 2015 ዓ.ም እና በኮ/መ/ቁ/137434 በ27/11/15 ዓ.ም በመጋቢት 05 ቀን 2016 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በቀድሞ አቃቂ ቃሊቲ ከ/ከተማ ወረዳ 09 በአሁኑ ሸገር ከተማ ሳይት ፕሮጀክት 17 ብሎh 505 የቤት ቁጥር 505/62 የሆነ በወ/ሮ ፅዮን ዜና ስም በካ/ቁ/አ/ቃ/958/6/80612/00 የተመዘገበ የቤቱ ስፋት 58.76 ካ/ሜ የሆነ ባለ አንድ መኝታ ኮዶሚኒዬም የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 1,338,446.10 (አንድ ሚሊዮን ሦስት መቶ ሰላሳ ስምንት ሺህ አራት መቶ አርባ ስድስት ብር 10/100) የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ግንቦት 8 ቀን 2016 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬከቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬከቶሬት ሐራጅ ከፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከጠ/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ዳ/ ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ብቻ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት። የፍ/አፈ/ዳይሬክቶሬት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።

በፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት

Save Tender