የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 05/2016
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የማዕከላዊ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የማዕከላዊ ዕዝ ጠ/መምሪያ ለ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተገለጸው በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ሎት 1. የተለያዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫ ጎማና ባትሪ ዕቃዎች
ሎት 2. የተለያዩ የኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎች
ሎት3. የተለያዩ የጀኔሬተርና ዳቦ ማሽን መለዋወጫ ዕቃዎች
ሎት 4. የተለያዩ አላቂ የጋራዥ መርጃ ዕቃዎች
ሎት 5. የተለያዩ አልባሳት
ሎት 6. የተለያዩ /የፈርኒቸር/የሆስፒታል VIP አልጋዎችን ጨምሮ
ሎት 7. የተለያዩ የቢሮ የጽሕፈት ዕቃዎች
ሎት 8. የተለያዩ የቢሮ የጽዳት ዕቃዎች
ሎት 9. የተለያዩ የሥልጠና ዕቃዎች
ሎት 10. የተለያዩ የኮንስትራክሽን ዕቃዎች
በዚህም መሠረት በዘርፉ የተሰማሩ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ ሠርተፍኬተ፣ የቫት ሠርተፊኬት እና የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸውን ይጋብዛል። ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መመሪያና ዝርዝር ሰነድ የያዘ 100.00 ብር /አንድ መቶ ብር/ በመከፈል ዘወትር በስራ ሰዓት በጅማ ከተማ ሳሪስ በሚገኘው የመከላከያ ካምፕ ቅጥር ግቢ ውስጥ የማዕከላዊ ዕዝ ግዥ ጊዜያዊ ቢሮ የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ የጨረታ ሰነድ በመግዛት በቢሮው ወደ ተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ጨረታው ሚያዝያ 18/2016 ዓ.ም ከሰዓት 8፡30 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከሰዓት 9፡00 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- ስልክ ቁጥር 09-13-49-63-59/09-14-00-65-95
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የማዕከላዊ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ
