የጨረታ ማስታወቂያ
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲኒማ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት
የአዲስ አበባ ሲኒማ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የ2015 በጀት አመትን
በጋፕ የተሰራን ሂሳብ ሪፖርት ወደ IFRS ለመቀየር በመስኩ ልምድ ያላቸው ድርጅቶችን ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ሎት 1- የአዲስ አበባ ሲኒማ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት የ2015 በጀት አመት በጋፕ የተሰራውን
የሂሳብ ሪፖርት ወደ IFRS መቀየር፤
ስለሆነም ተጫራቾች፡-
1. የኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣
2. የመንግስት ልማት ድርጅቶች በGAP የተሰራውን ወደ IFRS በመለወጥ የሰራና የስራ ልምድ ያለው ሆኖ ማስረጃ የሚያቀርብ፣
3. በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር መከፈላቸውን የሚያረጋግጥ በግብር ሰብሳቢ የተሰጠ ማስረጃ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
4. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ለመሆናቸው የምስከር ወረቀት /TIN NO/ ማቅረብ አለባቸው፤
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 2000.00 /ሁለት ሺህ ብር/ በአዲስ አበባ ሲኒማ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት ስም CPO በማሰራት ከኦርጅናሉ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የመወዳደሪያ ሰነድ ቢሮ ቁጥር 4 በመቅረብ የማይመለስ ብር
200 /ሁለት መቶ ብር እየከፈሉ መውሰድ ይችላሉ፡፡
7. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ መድረግ እና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶችን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ለመጀመሪያ ጊዜ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለio የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 7 በመቅረብ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
9. ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
10. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ላይ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን እና አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው፡፡
11. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
አድራሻ፡-ፒያሳ ሲኒማ ኢትዮጵያ ውስጥ
ስልክ ቁጥር:- 0111-57-04-67/ 0111-57-04-69
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲኒማ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት
