Tender Detail

Tender Details

  • Deadline18 Apr 2024, 2:20 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Organizational

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


በፍ/ባለመብት እነ ወ/ሮ ዘለቃሽ አበራ / እና በፍ/ባለዕዳ ወ/ሮ አሰገደች አማረ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 54090 በ21/2/2012 ዓ.ም እና መ/ቁ 78346 በ26/4/2015 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በጉለሌ/ከ/ከተማ ወረዳ 7 የቤ.ቁ 898 የሆነው መኖሪያ ቤት ዋናው ቤትና ሰርቪስ ቤቶች ፍርድ ያረፈበት ቤት መብት ያልተፈጠረለት ካርታ የሌለው በጂአይኤስ ላይ ያለው የቦታው ስፋት 248 ካ/ሜ የውስጥ ለውስጥ መንገድ 20 ካ/ሜ የሚነካው የተጠቀሰው የቦታ ስፋት ለካርታ ስራ እንደ ማስረጃ የሚያገልግል ሲሆን በዚህ የውርስ ግቢ ውስጥ 5 ክፍል ቤት እና ማዕድ ቤት ያለ በሐራጅ የማይሸጥ መሆኑ ታወቆ የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር1,285,500 (አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ አምስት መቶ ብር) ሆኖ የትራንዛከሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ግንቦት 5 ቀን 2016 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ በ8፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬከቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬከቶሬት ሐራጅ ከፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከጠ/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡

በተጨማሪ ተጫራቾች ካፒታል ጌይን እና ታከስ ስምን ይዛወርልኝ የሚልን ጥያቄ፣ሐራጁ ጐድቶኛል የሚሉ ጥያቄዎችን ዳይሬከቶሬት የማያስተናግድና በችሎት የሚጠየቅ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት

Save Tender