የሐራጅ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት እነ አቶ ቴዎድሮስ ባህሩ እና በፍ/ባለዕዳ እነ ወ/ሮ እህተማርያም በቀለ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር289577 በ15/9/2015 ዓ/ም እና በመ/ቁ 301280 በ9/2/2016 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በቀድሞ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 8 በአሁኑ ለሚኩራ ከ/ከተማ የቤ.ቁ አዲስ የካርታ ቁጥር ቦሌ8/75/6/93700/00 ተመዝግቦ የሚገኘው ይዞታ መለያ ቁጥር AA000060809451 የሆነው ቦታው ስፋት 618 ካ/ሜ የቦታው አገልግሎት ለንግድ (ድርጅት) የሆነው ቤት የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 51,596,442(ሃምሳ አንድ ሚሊዬን አምስት መቶ ዘጠና ስድስት ሺ አራት መቶ አርባ ሁለት ብር) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ግንቦት 6 ቀን 2016 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ በ5፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡ የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመወሰድ መጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ C.P.O የሚያመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ዳ/ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀን ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡ የፍ/አ/ዳይሬክቶሬት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም
ዳይሬክቶሬት
