የጨረታ ማስታወቂያ
መቄዶኛ የበጎ አድራጎት ማህበር በቅጥር ግቢው ውስጥ የሚገኙትን ያገለገሉና ቁሳቁሶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል ቁሳቁሶቹም ወንበሮችና ተሽከርካሪ ወንበሮች ጎማዎች የተለያየ መጠን ዓይነት ያላቸው እንጨት ነክ ዕቃዎች ጂፕስም ቦርዶች ለኮርኒስ ያገለገሉ ሶፋዎች የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች የመኪና መለዋወጫዎች ከስብሰባ አዳራሽ የተፈቱ አዳዲስና አሮጌ የስብሰባ አዳራሽ ወንበሮች ለቀርከሃ አልጋ መወጠሪያ የተሠሩ ሸራዎች የኮርኒስ መበራት ማቀፊያዎች (ፍሎረሰንት) የተለያዩ ቁርጥራጭ አሉሚኒየሞችና ጠፋጣፋ የፕላስቲክ ኮንዲዩቶሮች ናቸው።
በመሆኑም መጫረት የሚፈልጉ ተጫራቾች አዲስ አበባ ከተማ ለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 (በተለምዶ አያት ኮንዶሚኒየም ከጠበል መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት) በሚገኘው በማዕከሉ ዋና መሥሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ሲሆን ተጫራቾች ቁሳቁሶቹ በሚገኙበት ቦታ በመገኘት ከተመለከቱ በኃላ በማዕከሉ የጠቅላላ አገልግሎት ክፍል ድረስ በመምጣት ብር 200 በመክፈል የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 14 ቀናት ክፍት ሆኖ ቆይቶ በ15ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ5፡00 ሰዓት ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
ነገር ግን 15ኛው ቀን ዕሁድ ወይም ብሔራዊ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
ድርጅቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 8131 ወይም 0930-79-64-13 ወይም 0975-26-41-59 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
መቄዶኒያ የበጎ አድራጎት ማህበር
