Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Conformity Assessment Enterprise -ECAE (የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት)
  • Address Megenagna, Addis Ababa, Ethiopia, Phone: 011-8-69-50-39
  • Websitehttps://eas-eth.org/
  • Deadline15 Mar 2024, 2:16 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Organizational

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር - ኢ.ተ.ም.ድ /ብግጨ/003/16

Ethiopian Conformity Assessment Enterprise -ECAE (የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት)


የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት OILM CAST IRON WEIGHT በሀገር ውስጥ ማምረት የሚችሉ ድርጅቶችን በመጋበዝ አስመርቶ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች:-

1. በሥራ መስኩ ሕጋዊ የስራ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትንና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ።

2. የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነትን የምዝገባ ወረቀትና የግብር መለያ ቁጥር (Tin No) ያላቸው መሆኑን የሚያሳይ

ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

4. የዘመኑን ግብር የከፈሉና እንዲሁም በመንግስት መ/ቤቶች በጨረታ ለመሳተፍ እንደሚችሉ ከፌዴራል ወይም ከክልል ግብር ሰብሳቢ መ/ቤት ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው። በተጨማሪም ተጫራቾች በመንግስት መ/ቤቶች ጨረታ እንዳይሳተፉ የታገዱ መሆን የለባቸውም።

5. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ድርጅቱ ዋና መ/ቤት ግዥና አቅርቦት ቢሮ በመገኘት ህጋዊ ሠነዶችን በመያዝ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ።

6. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንከ ዋስትና አስፈላጊ ከሆኑ የጨረታ ሠነዶች ጋር በማካተት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

7. የጨረታ ሠነዱን በታሸገ ፖስታ አግባብ ባለው አካል በመፈረም ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው።

8. ተጫራቾች በተሰጠው ስፔስፊኬሽን መሠረት የማምረት ብቃታቸውን የሚሳይ ቴክኒካል ፕሮፖዛል እንዲሁም ሚዛኑን የሚሰሩበትን ዋጋ የያዘ ፋይናንሺያል ሠነዶችን በማዘጋጀት በአንድ ፖስታ አሽገው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

9. የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሳጥኑ በ16ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ይታሸግና በዕለቱ በ4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና አቅርቦት ቢሮ ይከፈታል። ሆኖም 16ኛው ቀን የሕዝብ በዓል የሚከበርበት ቀን ወይም የዕረፍት ቀን ከሆነ ጨረታው የሚከፈተው በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል። ተጫራቾች ጨረታው ሲከፈት በቦታው ባይገኙ የጨረታ መከፈት ሂደቱን አያስተጓጉለውም።

10. ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን አንስቶ ለ60 ቀናት ይሆናል።

11. የጨረታው ውጤት አሸናፊ እንደታወቀ ተሸናፊ ድርጅቶች ያስያዙት ቢድ ቦንድ ወዲውኑ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

12. የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ያሸነፈበትን ዋጋው 10% የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና በማቅረብ ውል ይፈራረማል።

13. ተጫራቾች ትከከለኛ አድራሻውንና ሥማቸውን በመግለጽ በመጫረቻ ሰነዳቸው ላይ መፈረምና ማህተም ማድረግ

አለባቸው። ማህተም ያልተደረገና ያልተፈረመ ሰነድ ከውድድሩ ውጭ ይሆናል።

14. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ከማስገባታቸው በፊት የጨረታ ሠነዱን በጥንቃቄ ማንበብ ይገባቸዋል፤ በጨረታ ሠነዱ ላይ የተቀመጡትን መመሪያዎች አለመተግበር ከጨረታው ያሠርዛል።

15. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011-8-69-50-39 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

16. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። አድራሻ፡- የኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት ስልክ 011-8-69-50-39

ፓ.ሣ.ቁጥር:- 11145 አዲስ አበባ

የኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት

Save Tender