የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር ት/ክ/ኤ/አ011/2015
የትግራይ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት
የትግራይ ክልል ኤሌክትሪከ አገልግሎት ለተለያዩ ተሽከርካሪዎች የሚውሉ የተለያዩ ዓይነትና መጠን ያላቸው ጐማዎች፣ ባትሪዎችና እና የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ዝርዝሩም እንደሚከተለው ነው፡፡
|
ተ.ቁ |
የዕቃዎች ዓይነትና መጠን |
ብዛት |
|
ሎት 1 |
የተለያዩ ዓይነት የተሽከርካሪዎች ጎማ ከነካላማደሪያውና ፍላፕ እንዲሁም ራድያል ጉማ (7.50x16 8.25x17:12.00x20 10.00x20) |
978 |
|
|
የተለያዩ ዓይነት የተሽከርካሪው ባትሪ (12V/150A 12v/120A 12V/70A |
88 |
|
ሎት 3 |
የተለያዩ ዓይነት የተሸከርካሪ ዕቃዎች/ፍልትሮዎች/ብረክ ፓድ እና ብሬክ ሹ |
1411 |
1. በጨረታው መሳተፍ ያለባቸው ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት፣ የዘመኑ ግብር የተከፈለበትን የታደሰ ንግድ ፈቃድ የምስክር ወረቀት ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
3. አድራሻ፡- መቐለ ከተማ ፕላኔት ሆቴል ወረድ ብሎ በሚገኘው የትግራይ ከልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት መ/ ቤት 3ኛ ፎቅ ግዥና ፋሲሊቲ ቢሮ ቁጥር 31፣
4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት ለሎት 1 እና ለሎት 3 ለእያንዳንዱ ሎት የገንዘብ መጠን ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ እና ለሎት 2 ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ/ በታወቀ ባንክ በተረጋገጠ ቼከ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንከ ጋራንቲ በትግራይ ክልል ኤሌከትሪክ አገልግሎት ስም ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ኦሪጅናል እና ኮፒ በማለት በተለያዩ ፖስታ በማሸግ በአንድ ፖስታ በማድረግ ጨረታ ቁጥር ምልክት በማድረግ ት/ክ/ኤ/አ/01/2015 የሚል ምልክት በማድረግ እስከ መጋቢት 18 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ቢሮ ቁጥር 31 ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
6. ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
7. ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
8. ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልከ ቁጥር +251-342406712 መደወል ይችላሉ፡፡
የትግራይ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት
