Tender Detail

Tender Details

  • Deadline20 Mar 2024, 12:30 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Organizational

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 የትምህርት ብልጭታ የመ/ደ/ት/ቤት ለ 2016 ዓ.ም የበጀት ዓመት ለአገልግሎት የሚውሉ የፅዳት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ ቋሚ ዕቃዎች ፣የስፖርት ትጥቅ ፣ አላቂ የትምህርት ዕቃዎች ፣አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ፣ ልዩ ልዩ መሳሪያዎችን ፣ አላቂ የህከምና ዕቃዎች ፣የፕላንት ማሽነሪ ጥገናና ሰርቪስ፣ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል ፡፡ በዚህ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተለውን ሁኔታ ማሟላትና ማቅረብ አለባቸው ።

1.በአቅራቢነት የተመዘገቡበትን የምዝገባ የምሰከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2. ተጫራቾች በተሰማሩበት የንግድ የዘርፍ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና ዋናውን በማሳየት ኮፒውን ማያያዝ አለባቸው ፡፡

3.የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ሰርተፊኬት) ያለውና ቫት ተመዝጋቢ የሆነ ::

4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡

5. ተጫራቾች ባሸነፏቸው ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች የሁለት ዓመት ዋስትና እና የተለያዩ የፕሪንተርና የፈቶ ኮፒ የማባዣ ቀለሞች የአንድ ዓመት ዋስትና መስጠት አለባቸው፡፡

6. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ዕቃ አይነት ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡

7. ተጫራቾች ያቀረቡትን አጠቃላይ ዋጋ 2% ፐርሰንት ያልበለጠ /በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡

8. ተጫራቾች ያሸነፉትን ዕቃ ዋጋ 10% በሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡

9. በሚያቀርቡት የዕቃ ዋጋ VAT 15% ተሰልቶ መካተት ይኖርበታል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን VAT እንደተካተተበት ተደርጎ ይወሰዳል።

10. ተጫራቾች የገዙትን የጨረታ ሰነድ ኦሪጅናል ላይ ሞልተው በታሸገ ፖስታ ላይ ማህተም በማድረግ ከ1ኮፒ ጋር በፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 3 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡

11. የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመ/ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 3 ውስጥ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የመከፈቻው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀናት ይከፈታል።

12. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡

13. መ/ቤቱ የሚጫረተውን ዕቃ ብዛት እንደ አስፈላጊነቱ 20% በመጨመር ወይም በመቀነስ ማዘዝ ይች፡

14. ተጫራቾች ያሸነፉትን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት የጉልበት ወጪ በተቋሙ ቅጥር ግቢ በሚገኘው ንብረት ክፍል ማድረስ አለባቸው፡፡

15. ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የተጫራች ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር፡- 011 1 26 62 73/ 0111 58 57 06/

አድራሻ ፡- አዲስ አበባ ሬስቶራንት ወረድ ብሎ የአራዳ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት በወረዳ 05 የትምህርት ብልጭታ የመ/ደ/ት/ቤት

በአራዳ ክ/ከተማ ትምህርት መምሪያ የትምህርት ብልጭታ የመ/ደ/ት/ቤት

Save Tender