ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር፡- ዕ.ዕ.ት.ድ/አቅ/007/16
ያገለገሉ እንዲሁም ለረጅም ጊዜ የተቀመጡ አዲስ መለዋወጫ፣ የተለያየ መጠን
ያላቸው ቡሎና ቡሎን ሽያጭ
ድርጅታችን በ2016 በጀት ዓመት የተለያዩ ያገለገሉ እንዲሁም ለረጅም ጊዜ የተቀመጡ አዲስ መለዋወጫ ዕቃዎች እና ሞተሮች የተለያየ መጠን ያላቸው ቡሎና ቡሎን ባሉበት ሁኔታ በድጋሜ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሰረት ተጫራቾች፡-
1. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ለሎት 1 (Store 1) 1.1 ቶዮታ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ 1. (Store 1) 1.2 መርቸዲስ ብር 30000 /ሶስት መቶ ብር/ ለ ሎት 1 (Store 1) 1.3 አይፋ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ ለሎት 11 ( store 2) ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/፣ ለሎት III (Used sparepart) ብር 150.00 /አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ እና ለሎት IV (Fixed asset) ቋሚና አላቂ ንብረቶች ብር 150.00 / አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ በመክፈል አቃቂ ቃሊቲ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ከፋይናንና ሂሳብ ዳይሬክቶሬት መግዛት ይችላሉ፡፡
2. ተጫራቾች በአካል በመቅረብ የንብረቶቹን ይዘት በመመልከት ከዚህ ደብዳቤ ጋር በአባሪነት በየሎቱ በቀረበው የዕቃ ዝርዝርን መሠረት በማድረግ የሚወዳደርበትን ነጠላ ዋጋ (Unit price) እንዲሁም ጠቅላላ ዋጋ (Total Price) በግልፅ በማስቀመጥ ከነቫቱ ተ.እታ ጨምሮ በመሙላት እስከ መጋቢት 27 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎኘ በአቅርቦትና ፋሲሊቲ ማኔጅመንት ዳይሬከቶሬት ለዚሁ ጨረታ
አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
3. በተጫራች የሚቀርብ የነጠላ ዋጋ ማቅረብያ ሰነድ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፡፡
4 ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሎት በመጥቀስ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ/ ለ ሎት 1 (1.1) ብር 10.000.00 /አስር ሺህ ብር/ : ለ ሎት 1 (1.2 መርቸዲስ) ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ ለ ሎት 1 (1.3 አይፋ) ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ ለ ሎት II (store 2) ብር 10.000.00 /አስር ሺህ ብር እና ለ ሎት III (Used sparepart 1) ብር 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር እና ለሎት IV (Fixed asset) ቋሚና አላቂ ንብረቶች ብር 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
5. ያላሸነፈ ተጫራች ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ውጤቱ እንደተገለፀ ወድያውኑ 100% ተመላሽ ይደረግለታል፤
6. ጨረታው መጋቢት 27 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚህ ዕለት ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የጨረታው ቀን
የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተገለፀው ቦታና ሁኔታ ይከፈታል፡፡
7. የጨረታ አሸናፊ ውጤት እንደተገለጸለት በግንባር ቀርቦ የተዘጋጀውን ውል በመፈረም በ15 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ንብረት ማንሳት ይኖርበታል። በተጠቀሰው ቀናት ባያነሳ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፣
8. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ
ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ :
* በስልከ ቁጥር on 4 39 00 75/35 92/15 69/011 439 10 27
* ፋክስ 39 63 36/0114 74 71 41 ፖ.ሳ.ቁ. 2562 አዲስ አበባ መጠየቅ ይችላሉ
ዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት
