የተተው ዕቃዎች ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ግ-372016 ጨረታ
በኢትዮጵያ ጉምሩከ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩከ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስመጪዎች በጉምሩከ አዋጅ ቁጥር 859/2006 እና በተሻሻለው የጉምሩከ አዋጅ ቁጥር 160/2011 መሰረት የተተው ወይም የተወረሱ ዕቃዎችን በእቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 መሰረት የተተው የተወረሱ ንብረቶችን ማለትም ROUND STEEL KADAI PP CUP! PISTONS KIT FOR TWO & THREE WHEELER, STEERING KNUCKLE BUSHING FOR TRUCK, LED SURFACE PANEL LIGHT, WHITE BOARD WITH STAND & WITH OUT STAND, DOCUMENT TRAY & OTHER OFFICE STATIONARY ITEMS, BLACK SLATE STONE TILE, MOZIC CERAMIC MATT, USED TOYOTA YARIS ENGINE WITH GEAR BOX A LADY & MEN SHOES እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በዚህም መሠረት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚገልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያJሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑ
ይፈልጋል:: በዚህም መሠረት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
1. ተጫራቾች የዕቃዎችን ዝርዝር፣ ዓይነት፣ ብዛት፣ የጨረታ ሰነድ እና መመሪያ መግለጫ እንዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ዘወትር ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 6፡00 ከሰዓት በኋላ በቀኑ 7፡00 እስከ ቀኑ 10፡30 እና ዓርብ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀኑ 5፡00 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡ 30 እስከ ቀኑ 10፡30 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀኑ 5፡30 የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ/ በመክፈል ከቅርንጫፍ ጽ/ቤት ገቢ ሂሳቦች ቡድን መውሰድ ይችላሉ፡፡
2. ተጫራቾች በጨረታ ከሚሰጠው ዕቃ ጋር በዘርፉ የፀና ንግድ ፍቃድ ያላቸው፥ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ሆኖም ግምታዊ ከብር 500,000.00 በታች የሆኑ ማንኛውንም እቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታከስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ ሳያስፈልግ መወዳደር ይችላሉ፡፡
3. ማንኛውም ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ጨረታ ከመከፈቱ በፊት በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ተጫራቾች የሚያስይዙት CPO በቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስም ETHIOPIAN CUSTOMS COMMISSION MODJO BRANCH OFFICE በሚል ሲሆን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከአዲስ አበባ አዳማ እና ሞጆ ቅርንጫፎች መዘጋጀት አለበት፡፡ ተሳታፊዎች ዋጋ መሙላት የሚችሉት በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ተዘጋጅቶ ማህተም ያረፈበት ሰነድ ላይ ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በመግዛት የሚወዳደሩበትን ዕቃ አስቀድሞ ማየት ያለባቸው ሲሆን እቃውን ሳያዩ ለሚሞሉት ዋጋ ቅ/ጽ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም፡፡ በጨረታ ተሽጦ የተወሰደ እቃ ተመላሽ አይደረግም ለእቃውም የተከፈለ ገንዘብ አይመለስም፡፡
5 ግልጽ ጨረታ ተሳታፊ ተጫራቾችን እያንዳንዱን ዕቃዎች ለመግዛት የሚያቀርቡት የመጫረቻ ዋጋ የሞሉበት ሰነድ በተራ ቁጥር 2 የተግለጹትነ ማስረጃዎች ኮፒ እና ያቀረቡት የመጫረቻ ዋጋ 5% ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 8 ተከታታይ ቀናት እስከ የመጨረሻው ቀን ጠዋት 4፡45 ሰዓት ድረስ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማሰገባት ይቻላል፡፡ የጨረታ ሳጥን ከታሸገ በኋላ የሚመጡ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
6 የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ የወጣበት ቀንን ጨምሮ በ8ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡45 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ጠዋት 5፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለጨረታ በአዘጋጀው ቢሮ ውስጥ ይከፈታል.
7. ማንኛውም በግልጽ ጨረታ የሚሳተፍ ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ዋጋ መቀየር ወይንም የሌላ ተጫራቾችን ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ አሻሽሎ ማቅረብ አይችልም፡፡ በጨረታ ሽያጭ ውድድር ላይ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም፤ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ እራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይቻልም እና የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል፡፡
8. የግልጽ ጨረታ አሸናፊ ጨረታውን ስለማሸፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን እቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ አለበት፡፡ በ5(አምስት ) ቀናት ውስጥ ገንዘቡ ገቢ ካልተደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል፡፡
9. በተራ ቁጥር 8 በተቀመጠው ጊዜ ገደብ ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ አድረጎ ዕቃውን ያላነሳ/ ያልተረከበ እንደሆነ ለሚቆይበት ለተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ ይከፈላል፡፡ ሆኖም ዕቃው በ2 (ሁለት) ወራት ውስጥ ካልወጣ እንደተተወ ተቆጥሮ በጨረታ ሽያጭ ይወገዳል፡፡
10. አሸናፊ ተጫራች ዕቃዎችን ለመረከብና ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሁሉ ራሱ ይሸፍናል፡፡
11. ቅንጫፍ ጽ/ቤቱ ለጨረታ የአቀረበውን ዕቃ ብዛት ለመጨመርም ሆነ ለመቀነስ ሙሉ መብት አለው፡፡
በጨረታ ተሽጦ በጨረታ አሸናፈው የተወሰደ እቃ አይመለስም፡፡
12. ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ እቃዎችን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ወይም ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
13. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 022-236-9094 ላይ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
