የሁለተኛ ዙር ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት
የሁለተኛ ዙር ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በኮልፌ ቀራንዮ ከፍለ ከተማ በወረዳ 8 ከልል የሚገኙ የቀራንዮ መ/ዓለም ቁጥር 2 አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት 002/2016 ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ እቃዎች ለመግዛት ይፈልጋል።
ሎት 1 አላቂ የጽፈት መሣሪያዎችና መገልገያዎች፤ ሎት 2 የፅዳት እቃዎች መገልገያዎች፤ ሎት 3 የደንብ ልብስ፣ ሎት 4 ህትመት፤ ሎት 5 ቋሚ እቃዎች፤ ሎት 6 የተለያዩ ማሽነሪ እና ኮምፒውተር ጥገና፤ ሎት 7 የተለያዩ ጥገናዎች እና ቀላል ግንባታ ሥራዎች፤ ሎት 8 የላብራቶሪ እቃዎች ግዥ ለመፈፀም ስለምንፈልግ በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።
1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ ሠርተፍኬት ያላቸው፤
2. የአቅራቢዎች ምዝገባ የምስክር ወረቀትና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፤
3. ለመጫረት የሚያበቃ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የቀራንዮ መ/ዓለም ቁጥር 2 አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ሂሳብ ክፍል ቢሮ ቁጥር 01 በመምጣት ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመከፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
5. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ የጨረታ ማስከበሪያ ቼከ /CPO/ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታው ሳጥን እስከሚታሸግበት ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይችላሉ።
6. ጨረታው በ1ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚያው እለት በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በትምህርት ቤቱ አዳራሽ ይከፈታል።
7. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተጫራቾች በዚህ ጨረታ እንዲወዳደሩ እየተጋበዙ እንዲሁም ከአደራጃቸው አካል ለጨረታ ሰነድ በነፃ እንዲወሰዱ፤ በጨረታ ማስከበሪያ እና በውል ማስከበሪያነት የሚያገለግል በግልፅና በዝርዝር በተፃፈ የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።
8. ተጫራቾች በጨረታ ማስከበሪያነት የሚያገለግል የገንዘብ መጠን ሎት 1 - 2,000.00 ሎት 2-2,000.00 32,000.00 5-3,000.00 6-1,000.00 7-1,000.00 የጨረታ ማስከበሪያ ቼከ /CPO/ ማቅረብ አለባቹ። 4-2,000.00 8-1,000.00
9. በጨረታ ማስከበሪያነት የተያዘውን ሲፒኦ ወይም ቼከ በመውሰድ እና ተጫራቾች ውል እንዲዋዋሉ ከመ/ቤቱ ሲገለፅላቸው ያሸነፉበትን የዋጋ ድምር 10% በውል ማስከበሪያነት የሚያገለግል በመስሪያ ቤታችን ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
10. የግዥ ውል በሚፈፀምበት ጊዜ መ/ቤቱ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተመለከተውን የዕቃ ብዛት እስከ 20 በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።
11. ጨረታ ሰነዱ ላይ ከተዘረዘሩት ውጭ በጥራት የሚበልጥና የሚስተካከል ዋጋ ያለው ዕቃ በማቅረብ መወዳደር ይቻላል።
12. ተጫራቾች ናሙና እንዲያቀርቡላቸው የተመረጡትን ዕቃዎችን ናሙናው እስከ ግልፅ ጨረታ ማለቂያ ቀንና ሠዓት በፊት ማቅረብ አለባቸው::
13. ተጫራቾች ከት/ቤቱ የወሰዳችሁትን መደበኛ የጨረታ ሰነድ በእናንተ የሚሞሉ ከፍሎችን በመሙላት ተመላሽ ማድረግ ግዴታ መሆኑን እናሳውቃለን።
14. አንድ ተጫራች ሌላው ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
15. ትምህርት ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 በጦርኃይሎች በሆላንድ ኤንባሲ ቀራንዮ አደባባይ ወደ ቀራንዮ በሚወስደው መንገድ በስተቀኝ በኩል ስልክ ቁጥር፡- 011-8-33-69-84/09-67-77-87-65/09-13-98-13-37
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት
የቀራንዮ መ/ዓለም ቁጥር 2 አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
