ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር CCSE-BRANCE /002/2016
በኢፌዲሪ ጉምሩክ ኮሚሽን
በአፌዲሪ ጉምሩከ ኮሚሽን የሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት አገልግሎት ሲገለገልባቸው የቆዩ የኤሌከትሮኒከስ እቃዎች (ዴስክቶፕ ኮምፒውተር፣ ፕሪንተር፣ኮፒ ማሽን፣ ላፕቶፕ፣ ሞባይል እና ሌሎችም በግልጽ ጨረታ ሽያጭ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም ድርጅት ወይም ግለሰብ ተጫራች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርቦ መወዳደር ይችላል።
|
የጨረታ ቁጥር |
የጨረታው ሰነድ ሽያጭ የሚጀምርበት ቀን |
የጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት |
የጨረታው መክፈቻ ቀን እና ሰዓት |
|
CCSE-Branch /002/2016 |
መጋቢት 04/2016 |
መጋቢት 18 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት |
መጋቢት 18 ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት |
1. በጨረታ ሽያጭ ስርዓት ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራች በዘርፉ የጸና የታደሰ ንግድ ፍቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ስዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ ከጠዋት 1፡00-6፡00 እና ከሰዓት 9፡00-12፡00 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋት 1፡00- 5፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00(አንድ መቶ) ብር በመከፈል በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በመገኘት ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በግዥና ፋይናንስ ቢሮ በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይቻላል።
3. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ(5%) ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና CPO (ETHIOPIAN CUSTOMS COMMISSION SEMERA BRANCH OFFICE) ስም በባንክ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
4. ጨረታው ከመጋቢት 04/07/2016 እስከ መጋቢት 18/07/2016 ዓ/ም ለተከታታይ 15 ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆያል።
5. ጨረታ የሚካሄድበት ቦታ በሰመራ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በሀብት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ሲሆን ጨረታው መጋቢት 18/07/2016 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
6 የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 17/07/2016 ዓ/ም
7. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ተመላሽ የሚደረገው ላሸነፈበት ዕቃ ሙሉ ከፍያ ከፈፀመ እና የተከፈለበት ዕቃ ሙሉ በሙሉ ማንሳቱ ከተረጋገጠ በኃላ ነው። እንዲሁም ለተሸናፊ ተጫራቾች የጨረታው ውጤት በተገለጸ በሦስት /3/ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸው።
8. አሽናፊው ተጫራች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ አምስት /05/ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን እቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ያለበት ሲሆን ይህንን ባይፈጽም ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ዋስትና ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ተደርጎ እቃው በድጋሜ ለጨረታ የሚቀርብ ሲሆን ነገር ግን የእቃውን ዋጋ ገቢ አድርጎ እስከ 1 ወር ጊዜ ውስጥ እቃውን ያላነሳ እንደሆነ ለሚቆይበት ተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ የሚከፍል ይሆናል። ሆኖም እቃውን ከ ወር በላይ ከቆየ ለንብረቱ የከፈለው ዋጋ ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ሆኖ እቃው እንደተተወ ተቆጥሮ በሽያጭ ይወገዳል፡፡
9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይንም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
10. ተጫራቾች ተመሳሳይ የዕቃ ጠቅላላ ድምር ቢያቀርቡ ቃለ ጉባኤ በመያዝ በእጣ የምንለይ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
11. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነድ የተሰጠውን ዋጋ መለወጥ ማሻሻል ወይም ጨረታው ከተክፈት በኃላ ራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይቻልም።
12. አሸናፊው የሚለየው በጠቅላላ ድምር ስለሆነ የእያንዳንዱ እቃ ዋጋ ዝርዝር መሞላት አለበት፡፡
13. በጨረታ ለሚሸጥ ዕቃ የጨረታው ውጤት በደብዳቤ እንደተገለጸ ከአሸናፊው ጋር የሽያጭ ውል እንደተደረገ ይቆጠራል፡፡
14. አሸናፊው ተጫራች ዕቃዎቹን ባሉበት ሁኔታ በመረከብ፣ ለመረከብ እና ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን
ሁሉ ራሱ ይችላል፡፡
15. ቅ/ጽ/ቤቱ ለጨረታ የቀረበውን እቃ ብዛት ለመጨመርም ሆነ ለመቀነስ ሙሉ መብት አለው፡፡
ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃዳቸውን እና ለእያንዳንዱ ዕቃ የሚገዙበትን ዋጋ ሻትን /NAT/ጨምረው በዋጋ ማስገቢያ ቅጽ ላይ በመሙላት እና የጨረታ ማስከበሪያ ሰነዱን (CPO) በማካተት በታሸገ ኤንቨሎፕ
ሙሉ አድራሻቸውን እና የጨረታ ቁጥሩን በመጥቀስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን እስከ መጋቢት 18 ቀን 2016 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
ለተጨማሪ መረጃ ፦ስልክ ቁጥር 0333661567/0333662797/0914362075
በኢፌዲሪ ጉምሩክ ኮሚሽን የሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት
