በድጋሚ የወጣ ያገለገሉ ዕቃዎች የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር አዲስፋ/ግጨ/003/2016
በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ አርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ
በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ አርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን የተለያዩ የሚወገዱ ንብረቶች ማለትም፡-
* ያገለገሉ የመኪና እና የማሸነሪ ባትሪዎች
* የተለያዩ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች
* የብረት በርሜሎች
* ጀሪካኖች
* ያገለገሉ የአፈር ማዳበሪያ ውስጡ ፕላስቲክ ያላቸውና የሌላቸው ከረጢቶች
* የተቃጠለ ዘይት
* የተለያዩ ያገለገሉ ባለ ክር እና ባለ ሽቦ የመኪና እና የማስፕሪ ጐማዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው ለመወዳደር ፍላጐት ያላችሁ አካላት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መስፈርቶችን የምታሟሉ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ድረስ አዲስ አበባ ካዛንቺስ ዮናስ ጨርጨር ስጋ ቤት ወረድ ብሎ ተንዳሆ ግቢ አርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቀርባችሁ ለዚህ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ/ ከፍላችሁ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
1. ቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፍያ መለያ ቁጥር (Tin.No) ያላቸው፤በሚወዳደሩበት ዘርፍ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም በመንግስት መ/ቤት ግዢ ለመወዳደር እንደሚችሉ ከገቢ ሰብሳቢ ድርጅቶች ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. ተጫራቾች በጨረታ መመሪያው ላይ የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
3. የሚጫረቱበትን ዋጋ በእያንዳንዱ በጨረታ ሰነድ መሠረት እስከ 16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ
ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
4. ጨረታው በሁለት የታሸገ ፖስታ መቅረብ ያለበት ሲሆን በቴክኒካል ፖስታ የአስፈላጊ ሰነዶች ትክክለኛ ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ አብሮ መቅረብ አለበት፡፡
5. ጨረታው በ 16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ሊገኙ ፈቃደኛ በሆኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
6. ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) ባይገኙም ጨረታውን ከመከፈት አያስተጓጉሉም፡፡
7. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጹትን ነገሮች ማሻሻል ወይም መተው አይችልም፡፡
8. የጨረታው ተሳታፊዎች / አቅራቢዎች ከዚህ በላይ የተገለጹትን በአግባቡ ሳይፈፅሙ ቢቀሩ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ለፋብሪካው ገቢ ሆኖ ተጫራቹ ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
9. ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ከዚህ በታች በተገለፀው አድራሻ አዲስ አበባ ካዛንቺስ ዮናስ ጨርጨር ስጋ ቤት ወረድ ብሎ ተንዳሆ ግቢ አርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ በማስተባበሪያ ጽ/ቤት ስልክ ቁጥር፡ 0910147760/0912102754 በመደወል ወይም ዘወትር በስራ ሰዓት በግንባር በመቅረብ ማነጋገር ይቻላል፡፡
10. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ አርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ
