የ2ኛ ዙር ቤቶች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ PTC 1.7./27/11/06/2016
- የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በቦሌ ፍሬንድሽፕ ሳይት' በምስራቅ አጠቃላይ ሳይት እንዲሁም በቦሌ/ገርጂ ዘመናዊ መንደር ካስገነባቸው ቤቶች መካከል 132 አፓርታማ ቤቶች /ዘመናዊ ቤቶችን/ በጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ብ.ግ.ጨ/አገ/11/06/2016 መግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾችን አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል::
|
ተ ቁ |
ቤቶቹ የሚገኙበት ሳይት |
ብዛት |
ቤቶቹ የሚገኙበት ደረጃ /ዓይነት |
|
1 |
በምስራቅ አጠቅቅላይ ሳይት |
12 |
|
|
2 |
|
32 |
|
|
3 |
በቦሌ/ገርጂ ዘመናዊ መንገድ |
88 |
|
2. ኮርፖሬሽኑ ለሚያከናውነው የቤቶች ሽያጭ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን እና የመወዳደሪያ ተመን ዋጋ በአንድ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው::
3. ጨረታው የሚከናወነው በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነ-ሥርዓትና ይኸንኑ አስመልክቶ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን መመሪያ መሰረት ነው::
4. የተሟላ የጨረታ ሰነዶችን ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች ከየካቲት 25 ቀን 2016 ዓ.ም አስከ መጋቢት 24 ቀን 2016 ዓ.ም ቅዳሜን ጨምሮ ባሉት 30 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ 2፡00 እስከ 11፡00 ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 6፡00 ድረስ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በካሽ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድን ለገሐር በሚገኘው በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ::
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት በሚገኘው ዋና የመስብሰቢ አደራሽ 1ኛ ፎቅ ለዚሁ ታሽጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በመጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 30ኛው ቀን ወይም መጋቢት 24 ቀን 2016 ዓ.ም ቀን ከሰዓት 11፡00 ሰዓት ድረስ እንዲያቀርቡ ሆኖ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺ ብር) በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ሲ.ፒ.ኦ በፌደራል ቤቶች ኮፖሬሽን ስም - ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው:: ከጨረታው መክፈቻ ዕለትና ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፤ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጨረታ ሰነዱ
ክፍል 1 ላይ በተገለፀበት ቀንና ሰዓት ይከፈታል::
6. ተጫራቾች ቤቶቹን በአካል ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ማብቂያው ቀን ድረስ በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3:00 እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ቤቶቹ በሚገኙበት አድራሻ ድረስ በመቅረብና ለዚሁ ስራ በሚመደቡ ባለሙያዎች እና በሚወጣው ፕሮግራም መሰረት ቤቶቹን መመልከት ይችላሉ::
7. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ መረጃ
በስልክ ቁጥር 011-8-55-36-12 ወይም 011-8-55-36-17
0911-80-92-63 ወይም 0913-35-62-32 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
ዌብሳይት /website www.fhc.gove.et
P... P.O. Box 299 ፋክስ ቁጥር፦ 011-5-54-60-45/011-5-52-46-46
