Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ሸዋ ዞን የግሼ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት
  • Address , Phone: 033 89 90 102
  • Website
  • Deadline24 Apr 2024, 4:46 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Organizational

የግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ሸዋ ዞን የግሼ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት


በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የግሼ ወረዳ ግ/ጽ/ቤት ለግሼ ወረዳ ግ/ጽ/ቤት በሴፍትኔት ካፒታል በጀት ለመስኖ አገልግሎትን የሚውሉ ሎት 1. የውሃ እቃ፣ ሎት 2.የአትክልት ዘር፣ ሎት 3.የልማት መሳሪያ፣ ሎት 4.የደን ዘር፣ ሎት5.የችግኝ ውሃ ማጠጫ ይገዛልኝ ብለው በጠየቁት መሰረት በግልጽ ጨረታ ዘዴ አወዳድሮ ግዥውን ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

1. በዘመኑ የታደሰ አግባብ ያለው ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ያለው/ያላት፡፡

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ያላቸው፡፡

3. የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /የቫት/ከፋይነት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡ለመሆናቸውም የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች በግልፅ የሚነበብ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::

5.ተጫራቾች የሚጫረቱባቸውን እቃ ዝርዝር/እስፔስፍኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ ፡፡

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር ለእያንዳንዳቸው ሎቶች ማለትም ሎት 1. 80 ብር፣ ለሎት 2. 30 ብር፣ ለሎት 3. 60 ብር ለሎት 4. 30 ብር፣ ለሎት 5. 20 ብር በመከፈል ከዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 02 መግዛትና ማግኘት ይችላሉ፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 1 ፐርሰንት በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንከ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የሚሰጥ ሆኖ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም ከባንክ የተረጋገጠ Letter of credit ወይም በጥሬ ገንዘብ በመስሪያ ቤቱ የእለት ገንዘብ መሰብሰቢያ ሰነድ ማስያዝ አለባቸው፡፡

8.ተጫራቾች ለተጫረቱበት ጨረታ የጨረታ ማስከበሪያ 1% ሲያስይዙ ለየብቻው ማስያዝ አለባቸው፡፡

9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ መረጃውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በገንዘብ ጽ/ቤት በግዥ/ፋ/ን/አስ/ደ/በቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 6 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የጨረታው ማስታወቂያ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 30 ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነዱን በመግዛትና በመሙላት እስከ 3ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለበቸው::

10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 6 በ31 ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ይከፈታል፣ ተጫራቾች ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ከመከፈት አይታገድም፡፡

11. ጨረታውን ያሸነፈው አካል ውል ማስከበሪያ 10% በማሲያዝ ውል መግባት ይጠበቅባቸዋል ፡፡

12. ጨረታው በሎት መሆኑ ይታወቅ ፡፡

13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

14. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝረዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 1 9314 /033 89 90 102 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

15.ከላይ በተዘረዘረው ያልተካተተ ካለ በመመሪያው መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል ፡፡

16. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓላት ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ስዓት ታሽጎ በ3፡30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ሸዋ ዞን የግሼ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት

Save Tender