የጨረታ ማስታወቂያ አውቶቢስና ሌሎች የፋብሪካ ተረፈ ምርቶች ሽያጭ
ኤደን ቢዝነስ አክሲዮን
ኤደን ቢዝነስ አክሲዮን ማህበር ሁለት ቫን የሽያጭ መኪናዎችን፣ አንድ ኤፍ ኤስ አር መኪና፣አንድ ታታ አውቶቢስ እና ሌሎች በርካታ ብረታ ብረተቶችና ሌሎች የፋብሪካ ተረፈ ምርቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል:: በመሆኑም በዚህ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ሁሉ ማሟላት ያለባቸው መመዘኛዎች እንደሚከተለው ይሆናል::
1. ተጫራቾች ለሽያጭ የተዘጋጁትን ሁሉ በቦታው ተገኝቶ በማየት፣ የሚገዙበትን ዋጋ ሞልቶ በመፈረምና በታሸገ ፖስታ አድርጎ ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት በጨረታው ላይ መወዳደር ይችላሉ::
2. በዚህ የሽያጭ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ድርጅት የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ቫን መኪና 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር)፣ለኤፍ ኤስ አርና ለታታ አውቶቢስ 40,000.00 (አርባ ሺህ ብር) ለብረታ ብረቶችና ሌሎች የፋብሪካ ተረፈ ምርቶች 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) በሲፒኦ ወይም የባንክ ጋራንቲ በማስያዝ ግዥ ለመፈጸም መወዳደር ይችላል::
3. በዚህ ጨረታ ላይ የሚሳተፉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 300(ሶስት መቶ ብር)በመክፈል ከአ/ማህበሩ ጽ/ቤት ሾላ ገበያ አካባቢ ከሲግናል ወደ መገናኛ በሚወስደው መንገድ ላይ ሾላ የትራፊክ መብራት ለመድረስ 100 ሜትር ሲቀር ከሚገኘው ህብረት ባንክ ወይም ወጋገን ባንክ ፊትለፌት በሚገኘው ኮብል ስቶን መንገድ ትንሽ ገባ ብሎ ከሚገኘው ኢደን ህንፃ 3ኛ ፎቅ ቢሮ 307 ማግኘት ይችላሉ::
4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የሚጫረቱበትን ዋጋ የያዘ ፖስታ ይዘው በመቅረብ ከሰኞ እስከ አርብ ዘወትር በስራ ሠዓት እንዲሁም ቅዳሜ ግማሽ ቀን እስከ ቀኑ 6፡00 ሠዓት ድረስ በአክሲዮን ማህበሩ ዋና ፅ/ቤት በሚገኝበት ሾላ ገበያ አካባቢ ከሲገናል ወደ መገናኛ በሚወስደው መንገድ ላይ ሾላ የትራፊክ መብራት ለመድረስ 100 ሜትር ቀደም ብሱ ከሚገኘው ህብረት ባንክ ወይም ወጋገን ባንክ ፊት ለፌት በሚገኘው ኮብል ስቶን መንገድ ትንሽ ገባ ብሎ ከሚገኘው ኤደን ህንፃ 3ኛ ፎቅ ቢሮ 307 ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ:: ጨረታው በ11ኛው ቀን 4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን ልክ 4፡30 ይከፈታል::
5. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል/ሙሉ በሙሉ/ የመሰረዝ መብት አለው::
ለተጨማሪ መረጃ
በስልክ ቁጥር 0113691482/0932181803
ይደውሉልን ልናስተናግድዎት ዝግጁ ነን::
