Tender Detail

Tender Details

  • Company Nile Insurance Company S.C (ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ)
  • Address ዋናው መ/ቤት ለገሐር (ብሔራዊ ቲአትር አካባቢ) ሀብት ሥራ አመራር መምሪያ /22ኛ ፎቅ/ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0114-42 60 00
  • Websitehttps://nileinsurancesc.com/
  • Deadline01 Mar 2024, 5:39 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Organizational

የጨረታ ማስታወቂያ (ቁጥር 148/2016)

Nile Insurance Company S.C (ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ)


ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ

ጉዳት/አደጋ ደርሶባቸው ለደንበኞቹ ተገቢውን ካሣ ከፍሎ በውክልና የተረከባቸውን ልዩ ልዩ ተሽክርካሪዎች፣ የተለያዩ የተሽከርካሪ አካሎች! ኩባንያው ሲጠቀምባቸው የቆዩ ኮምፒዩተሮች እና ተዛማጅ እቃዎች፣ ወንበርና ጠረንጴዛዎች፣ ቶነሮች፣ ጀኔሬተሮች፣ የመኪና ባትሪዎች፣ የመኪና ጎማዎችን እና ልዩ ልዩ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::

የተሽከርካሪ የስም ማዛወሪያ፣ የጉምሩክ ቀረጥ፣ ግብር እና ሌሎች ዕዳዎችና ወጪዎች ቢኖሩ በአሸናፊው የሚሸፈኑ ይሆናል::

የተሽከርካሪ የስም ዝውውር በገዢ ምክንያት ከስድስት ወር በላይ ቢቆይ በዚህ ምክንያት ለሚመጣ ችግር ኩባንያችን ኃላፊነት አይወስድም::

አሸናፊ ተጫራች የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር (TIN No.) ማቅረብ ይኖርበታል::

  1. ንብረቶቹ የሚገኙበት የኩባንያው ሪከቨሪ አድራሻ፡-

❖ ገላን ሪከቨሪ ፡ ገላን ኖክ ፊት ለፊት

❖ ያገለገሉ ዕቃዎች የሚገኙት በኩባንያው ዋና መስሪያቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ

ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ንብረቶቹ በሚገኙበት አድራሻ በሥራ ሰዓት ሄዶ በማየት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድና የጨረታ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ከፍሎ መውሰድ ይችላል::

የጨረታ መነሻ ዋጋ 15% ቫት ያላካተተ መሆኑን እየገለጽን፤ ማንኛውም ተጫራች የሚጫረትበትን የእያንዳንዱን ምድብ እቃ ዋጋ (ቫት ሳይጨምር) በጨረታ ማቅረቢያ ቅፅ ላይ በመሙላት ለእያንዳንዱ ምድብ እቃ የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የመነሻ ዋጋውን 20% (ሃያ ከመቶ) በኩባንያው ስም በተዘጋጀ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የኢንሹራንስ ቦንድ ጋር በኤንቨሎፕ በማሸግ እስከ የካቲት 29 ቀን 2016 ዓ.ም. ከቀኑ 11 ሰዓት ድረስ ብቻ የኩባንያው ዋና መ/ቤት በሚገኝበት ጎተራ ምድር ቤት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላል:: Dilb

ማሳሰቢያ፡- አሸናፊ ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ 15% ቫት የሚጨመር መሆኑን እንገልፃለን::

ጨረታው የካቲት 30 ቀን 2016 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጎተራ በኩባንያው ዋና መ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ ከጠዋቱ በ3፡00 ሰዓት ይከፈታል::

ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ለተሸናፊዎች ሙሉ በሙሉ የሚመለስ ሲሆን ለአሸናፊዎች ግን ከሚገዙበት ዋጋ ጋር ይታሰባል:: ተጫራቾች ለተጫረቱበት ንብረት አሸናፊነታቸው ከተገለፀበት ዕለት ጀምሮ በአሥር ቀናት ውስጥ ክፍያውን አጠናቀው ንብረቱን ባያነሱ ያስያዙት ገንዘብ በመቀጫ መልክ ለኩባንያው ገቢ

ሆኖ አሸናፊነታቸው ይሰረዛል::

ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለተጨማሪ ማብራሪያ

በስልክ ቁጥር  011-442-14-99/09-11-82-05-76/ በመደወል መጠየቅ ይችላል::

ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ

Save Tender