Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢትዮጵያ አርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
  • Address , Phone: 011 55 86 80
  • Website
  • Deadline04 Mar 2024, 3:39 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Organizational

የንግድ ቤት የኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ

በኢትዮጵያ አርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን


1. በኢትዮጵያ አርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት የቤተ ክርስቲያኗ ንብረት የሆነውን የድርጅት ለክሊኒክና ለተለያዩ ንግድ የሚውል በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል::

2. ለቢሮ እና ለንግድ የሚከራየው ቤት አድራሻ፡- በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 የቤት ቁጥር 355፡-

➢ ስፋቱ 242.74 ካሬ ሜትር የሆነ ቴዎፍሎስ ሕንጻ ተብሎ በሚጠራው ሕንጻ ላይ የሚገኝ ነው::

3. ማንኛውም ተጫራች የሚጫረተውን ቤትና ዋጋ በሠንጠረዡ ላይ በተሰጠው ትይዩ ባዶ ቦታ ላይ ብቻ ማስቀመጥ አለበት::

4. መንግሥታዊ ድርጅት ካልሆነ በስተቀር ማንኛውም ተወዳዳሪ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታይ ሆኖ ከሚገለገልበት ደብር የድጋፍ ደብዳቤና የአባልነት መታወቂያ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት::

5. ተጫራች በጨረታው አሸናፊ ሆኖ ቤቱን ከተረከበ በኋላ የውኃና የመብራት ፍጆታ ራሱ ይከፍላል::

6. ድርጅቱ ለኪራይ ያቀረበውን ቤት በጨረታ ተወዳድሮ ለመከራየት የሚፈልግ ሰው ወይም ድርጅት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡ 30 እስከ 11፡00 ክፍሉን በአካል ቀርቦ በማየት ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር5ዐዐ.ዐዐ(አምስት መቶ ብር) ከፍሎ ሠነዱን በመሙላት በኢንቨሎፕ በታሸገ ፖስታ በድርጅቱ ጽ/ቤት ለዚሁ አለማ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት::

7. ተጫራቾች ነጋዴ ከሆኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድና የዘመኑ ግብር የተከፈለበት ደረሰኝ፣ ኢንቨስተር ከሆነ የኢንቨስትመንት ፈቃድ፣ የንግድ ማኅበር ከሆነ የመመስረቻ ጽሑፍ፣ የጤና ዘርፍ ከሆነ ሕጉ ከሚፈቅድለት የጤና ቢሮ የተሰጠ ፈቃድ፣ የሙያ አገልግሎት ሰጪ ከሆነ የሙያ ፈቃዱን ፎቶ ኮፒ ከዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል::

8. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ክፍል የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ብር10,000.00 (አሥር ሺህ ብር) በማስያዝ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዳቸው በባንክ በተረጋገጠ ቼክ(CPO) ከሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ጋር ዋናውን በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::

9. ጨረታው በ1ዐኛው ቀን ከቀኑ 10፡00 ተዘግቶ በማግስቱ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ከጠዋቱ በ3፡00 ሰዓት በድርጅቱ ጽ/ቤት ይከፈታል::

10. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

11. የጨረታ መነሻ ዋጋ እና ዝርዝር መመሪያ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይቻላል::

ለበለጠ መረጃ

በስልክ ቁጥር 011 55 86 80 ወይም 011 1 57 47 99

በድርጅቱ ጽ/ቤት በአካል ቀርበው ይጠይቁ።

Save Tender