Tender Detail

Tender Details

  • Company ቡና ባንክ
  • Address , Phone: 111 58 08 80
  • Website
  • Deadline05 Mar 2024, 12:47 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Organizational

አክሲዮኖች በጨረታ ለመሽጥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

ቡና ባንክ


ቡና ባንክ አ.ማ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በወጣው መመሪያ ቁጥር  FIS/01/2016 መሰረትየውጭ አገር  ዜግነት ካላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን ባለአክሲዮኖች የተረከባቸውን በቁጥር 10,824 የሆኑ አክሲዮኖች የአንዱ አክሲዮን ዋጋ ብር 100 ሆኖ፤ ጠቅላላ ዋጋቸው ብር 1,082,400.00 የሚያወጡ አክሲዮኖችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::

በመሆኑም የአንድ አክሲዮን የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 100.00 ሲሆን ፤ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ለመሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን::

1. ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያለው ግለሰብ ወይም ሙሉ በሙሉ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ባላቸው ባለአክሲዮኖች የተያዙ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፤

2. ተጫራቾች ማንነታቸውን የሚያረጋግጥ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፤ የታደስ መንጃ ፈቃድ ወይም ፓስፖርት ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ፤ ወይም ተጫራቾች ድርጅቶች ከሆኑ ድርጅቱ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት የጸደቀ የመመስረቻ ጽሁፍ እና የመተዳደሪያ ደንብ ወይም ሌላ ተቀባይነት ያለው ማስረጃ ዋናውን እና ኮፒ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፤

3. ተጫራቾች አንዱን አክሲዮን የሚጫረቱበትን ዋጋ በመግለፅ መግዛት የሚፈልጉትን ጠቅላላ የአክሲዮን ዋጋ 4ኛ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፤የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሳይያያዝ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፤

4. ተጫራቾች መግዛት የሚችሉት አነስተኛ የአክሲዮን ብዛት በቁጥር 500 እና የገንዘብ መጠኑ ደግሞ ብር 50,000/ሀምሳ ሺህ/ ሲሆን ፤ ከዚህ በታች የሆኑ አክሲዮኖችን ለመግዛት የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፤

5. አክሲዮኖች የሚሸጡት በተጫራቾች የሚሰጠውን ዋጋ በማወዳደር ሲሆን ፤ የተሻለ ዋጋ የሚሰጡ ተጫራቾች ለመግዛት በገለጹት ዋጋ እና የተጠየቁትን አክሲዮኖች ብዛት ልክ በቅደም ተከተል ቅድሚያ ይሰጣል:: ተጫራቾች ተወዳድረው የጨረታው አሸናፈ መሆናቸው በባንኩ ሲገለጽላቸው የተሻለ ዋጋ ለሰጠ

ተወዳዳሪዎች ቅድሚያ በመሰጠቱ ምክንያት ሊገዙት ከጠየቁት የአክሲዮኖች ብዛት የቀነሰ ቢሆንም በቀጣይ የተሻለ ዋጋ የሰጠ ተወዳዳሪ የተረፉ አክሲዮኖችን ባቀረበው ዋጋ የመግዛት ግዴታ አለባቸው፤

6. ከአንድ በላይ ተጫራቾች ተመሳሳይ ዋጋ ቢሰጡ እና ተራፊ አክሲዮኖች ሁለቱ ተጫራቾች ከጠየቁት የአክስዮን ብዛት ቢያንሱ ቀሪዎቹ አክሲዮኖች ተመሳሳይ ዋጋ ለሰጡ ተጫራቾች እኩል ይከፋፈላል፤

7. ተጫራቾች ሌሎች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተመስርተው ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፤

8. የጨረታው አሸናፊዎች ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ የጨረታው አሸናፊ መሆናቸው በተገለፀላቸው በ15 ቀን /በአስራ አምስት ቀናት/ ጊዜ ውስጥ ለባንኩ ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል:: የጨረታው አሸናፊ በዚህ ጊዜ ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ ለባንኩ ገቢ ካላደረጉ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፤

9. ለጨረታ የቀረቡት አክሲዮኖች በሙሉ በአሸናፊዎች ከተገዙ በኋላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች የጨረታው ውጤት እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል፤

10. ከላይ የተገለጹትን የሚያሟላ ተጫራች ለጨረታው የተዘጋጀውን የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ እስከ መጋቢት 05 ቀን 2016 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4 ሰዓት ድረስ በስራ ሰዓት ቦሌ ሩዋንዳ መዞሪያ በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ 4ኛ ፎቅ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቀርበው በመውሰድ እና በመሙላት በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ አሽገው ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፤

11. ጨረታው መጋቢት 05 ቀን 2016 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በእለቱ 4:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም የሚመለከታቸው ታዛቢዎች በተገኙበት ቦሌ ሩዋንዳ መዞሪያ በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ 4ኛ ፎቅ ላይ ይከፈታል፤

12. በሌሎች ህጎችና በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ መመሪያዎች የተደነገጉ ደንቦች በዚህ ጨረታ ላይ ተፈፃሚነት አላቸው፤

13. ባንኩ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ተጨማሪ ማብራሪያ ቢይስፈልግዎ በስልክ ቁጥሮ

+251 111 58 08 80 ወይም

+251 111 26 28 22 በደወል ይችላሉ

ቡና ባንክ

አዲስ አበባ

Save Tender