Tender Detail

Tender Details

  • Company Amanuel Mental Specialized Hospital (የአማኑኤል የአእምሮ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል)
  • Address Addis Ketema Sub city : Addis Ababa : Ethiopia, Phone: +25144199174
  • Websitehttps://www.amsh.gov.et/
  • Deadline28 Feb 2024, 3:40 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Organizational

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

Amanuel Mental Specialized Hospital (የአማኑኤል የአእምሮ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል)


የአማኑኤል የአእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለ2016 በጀት ዓመት ሎት 1 ላብራቶሪ ሬጀንቶች እና ሰፕላይ ግዥ፣ ሎት 2፣ የፈሳሸ ማስወገድ አገልግሎት ግዥ ፣ ሎት3 የፀረ ተባይ ርጭት የአገልግሎት ግዥ ኦት 4 በአዲስ አበባ ከተማ የደረጃ 4 ሆቴል የአገልግሎት ግዥ ሎት 5 የላውንደሪ ማሽን ጥገና የአገልግሎት ግዥ ሎት 6 የጋራዥ አገልግሎት ግዥ ሎት 7 የAC የቅድመ ብልሽት ጥገና እና የብልሽት ጥገና አገልግሎት ግዥ በጨረታ ቁጥር AMSH/006/2016 በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ፡

1 በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና በዘርፉ የተመዘገባችሁበትን የሚገልጽ ፍቃድ፡፡

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin/ያላቸው::

3. የዘመኑ ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው ማስረጃ፡፡

4. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 20,000 /ሀያ ሺህ ብር/ በሲ.ፒ.ኦ፣ በጥሬ ገንዘብ ወይም የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለበት

5. ሎት 1 ላይ የሚጫረቱ ተጫራቾች የታደሰ /EFDA/ ማቅረብ አለባቸው::

6. የጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና 90 ቀናት/ ዘጠና/ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን አለበት፡፡

7. ሪኤጀንቶች ለማቅረብ የሚሳተፉ ተጫራቾች የምታቀርቡት ሪኤጀንቶች ዝቅተኛ ማብቂያ ቀን /Expiration date/ ከአንድ ዓመት በላይ መሆን አለበት፡፡

8. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡

9 ተጫራቾች የአገልግሎት ዋጋችሁን ሆስፒታሉ ለዚህ ጨረታ ባዘጋጀው ሰነድ የድርጅታችሁን ማህተምና ፊርማ በማድረግ መሙላት ይኖርባችሆል

10 ሎት 2 እና ሎት 3 የምትወዳደሩ ተጫራቾች በዘርፉ ፈቃድ ያላቸው መሆኑን ከሚመለከተው ባለስልጣን ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው።

11 ማንኛውም ተጫራች ሀሣቡን በአንድ ፓስታ ውስጥ ወይም ብቻ ለብቻ ሁለት ቅጂዎች ቴክኒክ ዋናና ኮፒ እና ፋይናንሻል ሰናዳችሁን ዋናና ኮፒ በማለት እያንዳንዱ ገጽ ላይ የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፓስታ በአማኑ ኤል አእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆሲፒታል በግዥ ዳ/ዳ ቢሮ በተዘጋጀው በጨረታው ሣጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ትችላላችሁ።

12 ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ሆኖ በ15ኛው ቀን ላይ ከቀኑ 10፡30 የጨረታ ሣጥን ተዘግቶ በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ዳ/ዳ ቢሮ ጨረታው የሚከፈት ይሆናል። ጨረታው የሚዘጋበትና የሚከፈትበት ቀን የበዓላት ቀን ከሆነ የሚቀጥለው የስራ ቀናት የሚከፈትና የሚዘጋ ይሆናል።

13.ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በግዥ ዳ/ዳይሬክተር ቁጥር 71 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም  በስልክ ቁጥር 0118685387/0112788056  በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

*መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡

የአማኑኤል የአአምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

Save Tender