Tender Detail

Tender Details

  • Deadline26 Mar 2024, 1:57 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Organizational

የተተው ዕቃዎች ሽያጭ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ግ-34/2016


በኢትዮጵያ ጉምሩከ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስመጪዎች በጉምሩከ አዋጅ ቁጥር 859/2006  እና በተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 1160/2011 መሰረት የተተው ወይም የተወረሱ ዕቃዎችን በእቃ አወጋገድ መመሪይ ቁጥር 167/2012 መሠረት የተተው/የተወረሱ ንብረቶችን ማለትም

Roof brick roof casting heating element burner block fiber brick MONOLITHIC FOR INDUSTRIES REFACTIORY AL SIDE ARCH FIRE BRICKS እና ሌሎች የኝባታ ዕቃዎች ROUND STEEL KADAI PACKING MATERIAL PRINTED & NONE PRINTED CARTON SHEETS NONE PRINTED BANNER & NONE PRINTED CARTON SHEETS NONE PRINTED BANNER & TRUCK SPARE PARTS የሳይክል ከመነዳሪ እና የመኪና መለዋወጫዎች! 2&3 WHEELER መለዋወጫዎች FIRE HOUSE CABINET እና BOOSTER BATTERY CHARGER እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሠረት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያJሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

1. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር 1 ዓይነት ብዛት፣ የጨረታ ሠነድ እና መመሪያ መግለጫ እንዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ዘወትር ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 6፡00 ከሰዓት በኋላ

ከቀኑ 7፡00 እስከ ቀኑ 10፡30 እና ዓርብ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 5፡00 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡30 እስከ ቀኑ 10፡30 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 5፡30 የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመከፈል ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ገቢ ሂሳቦች ቡድን መውሰድ ይችላሉ፡፡

2. ተጫራቾች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር በዘርፉ የፀና ንግድ ፈቃድ ያላቸው : የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር! የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡

ሆኖም ግምታዊ ዋጋቸው ከብር 500,000.00 /በታች የሆኑ ማንኛውም ዕቃ ለመገዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሠርተፍኬት ማቅረብ ሳያስፈልግ መወዳደር ይችላሉ።

3. ማንኛውም ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ጨረታ ከመከፈቱ በፊት በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ተጫራቾች የሚያስይዙት CPO በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሥም ETHIOPIA CUSTOMS COMMISSION MODJO BRANCH OFFICE በሚል ሲሆን በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ከአዲስ አበባ፤ አዳማ እና ሞጆ :: ቅርንጫፍ መዘጋጀት አለበት ተሳታፊዎች ዋጋ መሙላት የሚችሉት በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ተዘጋጅቶ ማህተም ያረፈበት ሠነድ ላይ ብቻ መሆኑ ይኖርበታል።

4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በመግዛት የሚወዳደሩበትን ዕቃ አስቀድሞ ማየት ያለባቸው ሲሆን ዕቃውን ሳያዩ ለሚሞሉት ዋጋ ቅ/ጽ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም፡፡ በጨረታ ተሸጦ የተወሰደ እቃ ተመላሽ አይደረግም፣ ለእቃውም የተከፈለ ገንዘብ አይመለስም ፡፡

5. የግልጽ ጨረታ ተሳታፊ ተጫራቾች እያንዳንዱ ዕቃዎች ለመግዛት የሚያቀርቡት  የመጫረቻ ዋጋ የሞሉበት ሠነድ በተራ ቁጥር 2 የተገለጹተን ማስረጃዎች ኮፒ እና ያቀረቡት የመጫረቻ ዋጋ 5% ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO በኤንቬሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ8 ተከታታይ ቀናት እስከ የመጨረሻው ቀን ጠዋት 4፡45 ድረስ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይቻላል፡፡ የጨረታ ሣጥኑ ከታሸገ በኃላ የሚመጡ የመጫረቻ ሰንዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።

6. የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ የወጣበት ቀንን ጨምሮ በ8ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4:45 ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 5፡00 ላይ ተጫራቾቹ ወይምንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለጨረታ ባዘጋጀው ቢሮ ውስጥ ይከፈታል።

7. ማንኛውም በግልጽ ጨረታ የሚሳተፍ ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ዋጋ መቀየር ወይንም የሌላ ተጫረታቶችን ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ አሻሽሎ ማቅረብ አይችልም፡፡ በጨረታ ሽያጭ ውድድር ላይ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም፡ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ እራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይቻልም እና የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል፡፡

8. የግልፅ ጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ስለማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ አለበት፡፡ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ገቢ ካልተደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል፡፡

9. በተራ ቁጥር 8 በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ አድርጎ ዕቃዉን ያላነሰ) ያልተረከበ እንደሆነ ለሚቆይበት ለተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ ይከፍላል፡፡ ሆኖም ዕቃው በ2 /ሁለት/ ወራት ውስጥ ካልወጣ እንደተተወ ተቆጥሮ በጨረታ ሽያጭ ይወገዳል፡፡

10. አሸናፈው ተጫራች ዕቃዎችን ለመረከብና ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሁሉ ራሱ ይሸፍናል፡፡

11. ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለጨረታ የአቀረበውን ዕቃ ብዛት ለመጨመርም ሆነ ለመቀነስ ሙሉ መብትአለው። በጨረታ ተሸጦ በጨረታ አሸናፊው የተወሰደ እቃ አይመለስም፡፡

12. ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዕቃዎቹን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ወይም ዘዴ ከገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለተጨማሪ ማብራሪያ በሥልክ ቁጥር- 022-236-90-94 ላይ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

በገቢዎች ሚኒስቴር ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

Save Tender