የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 002/2016 ዓ.ም
Addis Ababa Revenues Bureau (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ)
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የመርካቶ ቁጥር 2 መ/ግ/ከ/ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለ2016 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ እና አላቂ የቢሮ ንብረቶችን ማለትም ሎት 1 የደንብ ልብስ፣ ሎት 2 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 3 የህትመት ውጤቶች፣ ሎት 4 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 5 ልዩ ልዩ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ ሎት 6 የመኪና መለዋወጫ እቃዎች፣ ሎት 7 የተለያዩ የጥገና መለዋወጫ እቃዎች ሎት 8 ቋሚ የአይቲ እቃዎች፣ ሎት 9 የቢሮ ምንጣፍ እና ፈርኒቸሮችን ወይም የብረት ውጤቶች ሎት 10 የታሸገ ውሃ አቅርቦት አገልግሎት እና የተዘረዘሩ እቃዎች አቅርቦት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ህጋዊ መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
1 የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ከሊራንስ፣ ጨረታ ላይ እንዲሳተፉ የሚያስችል ደብዳቤ፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ የተመዘገቡበትን ሠርተፍኬት እንዲሁም የግብር ከፋይ መለያ ሠርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
2 ተጫራቾች ለጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመከፈል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ልደታ መናፈሻ ፊት ለፊት በላይ ተከሉ ኬከ ቤት ጎን በሚገኘው ዊዝ ደም የገቢያ መዓከል አከሲዮን ማህበር መርካቶ ቁ.2 መ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት ህንፃ ላይ 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 705 ግዥ እና ፋይናንስ የሥራ ሂደት በአካል በመቅረብ የጨረታ ሠነዱን በጥሬ ገንዘብ መግዛት ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 7000.00 /ሰባት ሺህ ብር/ ለቋሚ እቃዎች እና ለሌሎች እቃዎች 5000.00/አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒአ /CPO/ ብቻ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ መርካቶ ቁጥር 2 መ/ግ/ከ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት (Addis Ababa City Government Revenues Bureau Merkato No. 2 Medium Tax Payers Branch Office) በሚል ስም በማሰራት እና ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሱ የህጋዊ ማረጋገጫ ሰነዶችን፣ ጥቃቅንና አነስተኛ ከሆኑ ከአደራጅ መሥሪ የቤቱ የተፃፈ ደብዳቤ እንዲሁም ዋጋ ያልተሞላበት የዋጋ ማወዳደሪያ ሰንጠረዥ የተወዳደራችሁበትን እቃዎች በመከበብ ወይም ምልከት በማድረግ ኦርጂናሉን እና ኮፒ 1ዋናውን ቅጅውን ለየብቻ መታሸግ ይኖርባቸዋል፡፡
4. የፋይናንሻል /ዋጋ ማወዳደሪያ ሰንጠረዥ ዋጋው ከነቫቱ ተሞልቶ ብቻውን በኦርጅናል እና ኮፒ /ዋናውና ቅጅ/ ለየብቻ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል።
5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሠነድ በድምሩ አራት ኤንቨሎፕ ኦርጂናልና ኮፒውን ወይም /ዋናውንና ቅጂውን ለየብቻ በሰም ወይም በሌላ ማጣበቂያ በማሸግ ከመ/ቤታችን በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ የጨረታ ማስታወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ቀን እስከ 10ኛው የሥራ ቀን ቅዳሜን ጨምሮ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
6. ተጫራቾች በተሳተፉበት አቅርቦት ላይ ለመ/ቤቱ ኮሚቴዎች ሳምፕል ማቅረብ ማለትም የጽህፈት፣ የጽዳት፣ የደንብ ልብስ፣ የመኪና እቃዎች እና ናሙና ለተጠየቀባቸው ፍላጎቶች ሁሉ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ እንዲሁም በቀላሉ ለማንቀሳቀስ የማይችል ልዩ ልዩ ቋሚ እቃዎች ናሙና ለመሥሪያ ቤታችን ኮሚታዎች በተጫራቾት ድርጅት ውስጥ በአካል ለማሳየት ፍቃደኛ መሆን ይጠበቅበታል፡፡
7. የጨረታ ሣጥኑ ጨረታው በወጣበት በ1ዐኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጽ/ቤታችን የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።፡ ሆኖም ጨረታ የሚከፈትበት ቀን ዓመት በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን 4፡30 ይከፈታል፡፡
8. አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
9. ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
10. የጨረታ ሳጥን ከተዘጋ ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
11. እኩል ውጤት ያገኙ ተጫራቾች ተጨማሪ የማወዳደሪያ ሃሳብ እንዲያቀርቡ ይደረጋል ለሶስተኛ ጊዜ እኩል ከሆኑ በእጣ እንዲለዩ ይደረጋል፡፡
12. የጨረታ መገምገሚያ ዘዴዎች በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በከፍል ሶስት እና ክፍል ስድስት በተጠቀሱት መሰረት ብቻ ይሆናል፡፡
13. ተጫራቾች ሁሉንም የመወዳደሪያ ሰነዶች ህጋዊ ስልጣን ባለው አካል ተፈርሞባቸውና የድርጅታቸውን ማህተም አርፎባቸው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
14. የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀን እና ለተጨማሪ 28 ቀን የሚቆይ ይሆናል፡፡
15. መሥሪያ ቤታችን ከአሸናፊ ድርጅቶች ጋር በጨረታ ሰነዱ ከተገለጸው የአቅርቦት መጠን ላይ ምንም የዋጋ ልዩነት ሳይኖር እስከ 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
16. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0112768962/0112732771 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ መርካቶ ቁጥር 2 መ/ግ/ከ/ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ
