የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 02/03/2016
ገላን የወንዶች አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የገላን የወንዶች አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2016 ዓ.ም ከዚህ በታች የተዘረዘሩ የተለያዩ የዕቃ ግዢዎችን ለመፈፀም አቅራቢ ድርጅቶች በጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
1. አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
2. አላቂ የትምህርት ዕቃዎች
3. የተለያዩ የጽዳት ዕቃዎች
4. የተለያዩ የደንብ ልብሶች
5. ቋሚ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት፡
1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
3. በመንግስት ዕቃ አቅራቢነት የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው
4. የዘመኑን ግብር የከፈሉ
5. ተጫራቾች የማይመለስ 300 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከት/ቤቱ ፋይናንስ ክፈል ቢሮ ቁጥር 2 መግዛት ይችላሉ፡፡
6. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነዱ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ ማህተም ስምና ፊርማቸውን በማኖር በታሸገ ኤንቨሎፕ /ኮፒና ኦሪጅናል በማለት/ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከ2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ በት/ቤቱ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
7. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000 /ሀምሳ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ /CPO/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
8. ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በወጣ
በ11ኛው የስራ ቀን በ4፡30 ሰዓት ይሆናል፡፡
9. ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ደራርቱ ት/ቤት አጠገብ ገላን የወንዶች አዳሪ
2ኛ ደ/ት/ቤት ስልክ 0114715895
ገላን የወንዶች አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
