ግስጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በ
በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የአዲስ ማሽንና መለዋወጫ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ከድርጅቱ የሚወገዱ የተለያዩ የብረት ፍቅፋቂ (ችፕስ) ፣ ካርትሬጅ እና የተቃጠለ ዘይት በጨረታ አወዳድሮ
መሸጥ ይፈልጋል::
በመሆኑም ተጫራቾች፡-
1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
2. በግብር ከፋይነት የተመዘገቡና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN NO) ያላቸው
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ኦሪጅናልና ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋው 2% ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
6. ተጫራቾች የማይመለስ 300 (ሶስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታውን ሙሉ ሰነድ
ከኢንዱስትሪው ንብረት አስተዳደር ቢሮ ዘወትር በስራ ሰዓት መውሰድ ይችላሉ::
7. መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳችሁን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ጨረታው ከወጣበት እስከ አስራ ስድስተኛው ቀን 4፡00 (አራት ሰዓት) ድረስ ብቻ ማስገባት ትችላላችሁ::
8. ጨረታው ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀን አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ16 (አስራ ስድስተኛው) ቀን የጨረታ ሳጥኑ 4፡30 ተዘግቶ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡45 ይከፈታል፡፡
መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ
የተጠበቀ ነው::
አድራሻ:- ሜክሲኮ አደባባይ ወደ ሣር ቤት በሚወስደው መንገድ ከኦላ ኢንጂነሪንግ ወደ ውስጥ 100 ሜትር ገባ ብሎ ያለው ግቢ
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +251115508685/+25115520565 ደውለው ቢጠይቁን መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የአዲስ ማሽንና
መስዋወጫ ማምረቻ ኢንዱስትሪ
